የሩስያ ዩክሬን ጦርነት አንደኛ ዓመት
ዓርብ፣ የካቲት 17 2015ማስታወቂያ
የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ዛሬ አንደኛ ዓመት ዛሬ ሲታሰብውሏ።በተለያዩ የአውሮጳ ከተሞች የሚገኙ ህንጻዎች በዩክሬን ባንዲራ ቀለሞች አሸብርቀው ውለዋል። ትናንት የተካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩስያ በዩክሬን የምታካሂደውን ውጊያ እንድታቆም እና ሠራዊቷንም ከዩክሬን እንድታስወጣ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ አጽድቋል። ሩስያ ግን የውሳኔ ሀሳቡን ፋይዳቢስ ስትል አጣጥላዋለች።ጦርነቱ የተጀመረበት እለት በመታሰብ ላይ ባለበት በዛሬው ቀን ሩስያ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች ላይ ጥቃት መሰነዘሯ ተሰምቷል። ትናንትም በዩክሬን ባካሄደችው ድብደባ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን አስታውቃ ነበር። ስለ ሩስያ ዩክሬን ጦርነት አንደኛ ዓመት መታሰቢያና የሩስያና የምዕራባውያን ፍጥጫ ስላስከተለው ስጋት የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን በስልክ አነጋግረነዋል።
ገበያው ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ