Eshete Bekeleቅዳሜ፣ ኅዳር 22 2016ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መግደሉን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ወነጀለ። ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በወረዳው ሦስት መንደሮች በሁለት ቀናት በፈጸሟቸው ጥቃቶች በትንሹ 36 ሰዎች መገደላቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲያፈላልግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቋቋመው ኮሚቴ የለያቸውን ሁለት የመጨረሻ እጩዎች ይፋ አደረገ። በሶማሊያ ላይ ተጥሎ የቆየው የጦር መሣሪያ ግዢ ማዕቀብ እንዲነሳ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ሲወስን ሶማሌላንድ ተቃወመች። የቅዳሜ የዓለም ዐበይት ዜናዎችን ያድምጡ!