1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስኬታችን ቁልፍ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 9 2014

በ2013 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ትምህርታቸውን ተከታትለው በከፍተኛ ውጤት ዩንቨርስቲዎችን የተቀላቀሉ ሶስት እንስት ተማሪዎች የዛሬ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች መሰናዶ እንግዶች ናቸው፡፡ በኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት አዳማ ቅርንጫፍ ትምህርታቸውን ተከታትለው በክልል ደረጃ በሴቶች ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ሲፈን ፊጣ፣ ሎቲ ያደታ እና ሃዊ ጣሰው ለቃለ ምልልሱ ቀርበዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4BPCU

ሲፋን በሂሳብ ትምህርት ከ100 100 በማስመዝገብ ብዙም የማይስተዋለውን ከባዱን ፈተና በማሳካት መነጋገሪያ ሆናለች፡፡ ከሲፈን ጋር በዝግጅቱ የቀረቡ ሁለቱ ተማሪዎችም በሴቶች ዘርፍ እንደ ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ የበቁ ቀዳሚ ተማሪዎች በመሆን ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. የክልሉ ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀውን የሜዳሊያ እና ገንዘብ ሽልማት ከክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተቀብለዋል፡፡
የ2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርታቸውን በአንድ ትምህርት ቤት ተምረው ስኬታማ መንገድን ከጀመሩት ጓደኛሞቹ ጋር የዶይቼ ቬለ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሱመያ ሳሙኤል ቆይታ አድርጋለች፡፡

ዘገባ: ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ: ሥዩም ጌቱ