1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርት

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች

ረቡዕ፣ ጥቅምት 24 2014

ንፁህ ገብሬ ፣ ፌቨን ሙላቱ እና በአምላክ ታመነ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ናቸው። ተማሪዎቹ በራሳቸው ጥረት እንዲሁም በቤተሰባቸው እና በመምህራኖቻቸው ድጋፍ ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓም የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/42X5U

«በቂ ዝግጅት አድርጌያለሁ» የምትለው ፌቨን ከዚህ ቀደም የተሰጡ ፈተናዎችን በመከለስ እየተዘጋጀች መሆኗን ትናገራለች። ንፁህ ደግሞ ወላጆች ልጆቻቸውን መደገፍ እና ለሴት ተማሪዎች እቤት ውስጥ ያለውን ጫና መቀነስ አለባቸው ትላለች። የድሬደዋ ቤተ መዛግብት እና መፃህፍት አስተባባሪ ኤርሚያስ ታደሰ ለዶይቸ ቬለ እንደገለፁት «በርካታ ሴት ተማሪዎች ከቤት የሚገጥማቸውን ጫና ተቋቁመው በመምጣት እያነበቡ ነው» ይላሉ።  የድሬደዋ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊዲያ መለስ እራሷ ከተፈታኞቹ መካከል ናት። ባላት ክፍት ጊዜ የ12ኛ ክፍል ሴት ተፈታኞችን አነጋግራለች። 

ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ