ማስታወቂያ
አለማቸው በዚህ በተያዘው 2014 ዓ.ም በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ለሚገኙ 50,000 ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያዎችን ማቅረብ ነው። የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ መስራች የሆነችው ሚካል ማሞ እንደምትለው ከሆነ የወር አበባ መቀበያ ሞዴስ ችግር በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል ብቻ ያለ ሳይሆን በከተማ ውስጥም በሰፊው ይገኛል። በርካታ ሴቶችም በወር አበባ መቀበያ እጦት ምክንያት መሠረታዊ ከሆነው የትምህርት ገበታቸው ይስጓጎላሉ። ይህ ብቻ አይደለም በተለይ አዳጊ ሴቶች ስለጉዳዮ ደፍረው ለማውራት አይደፍሩም። ይህም ዝምታ እንዲሰበር እና ችግሩ ላይ እንዲሰራ ለማሳየት የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሱመያ ሳሙኤል የወር አበባ መቀበያ ወደሚመረትበት ድርጅት ሄዳ ዘገባ አዘጋጅታለች።
ዘገባ: ሱሙያ ሳሙኤል
ቪዲዮ: ሰለሞን ሙጬ