1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

ውይይት

ዓርብ፣ ግንቦት 12 2014

በ2013 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በከፍተኛ ውጤት አጠናቀው ዩንቨርስቲዎችን ከተቀላቀሉ ሶስት ሴት ተማሪዎች ጋር የተደረገ ውይይት፦ ታዳጊዎቹ የተማሩት በኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት አዳማ ቅርንጫፍ ሲሆን በክልል ደረጃ በሴቶች ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገባቸውም ተሸላሚ ሆነዋል።

https://p.dw.com/p/4BSy5
DW The 77 Programm | GOM Diskussion
ምስል S. Getu/DW

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ምርጥ ሴት ተማሪዎች

በክልል ደረጃ በሴቶች ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ሲፈን ፊጣ፣ ሎቲ ያደታ እና ሃዊ ጣሰው ለቃለ ምልልሱ ቀርበዋል፡፡ ሲፋን በሂሳብ ትምህርት ከ100 100 በማስመዝገብ ብዙም የማይስተዋለውን ከባዱን ፈተና በማሳካት መነጋገሪያ ሆናለች፡፡ ከሲፈን ጋር በዝግጅቱ የቀረቡ ሁለቱ ተማሪዎችም በሴቶች ዘርፍ እንደ ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ የበቁ ቀዳሚ ተማሪዎች በመሆን ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. የክልሉ ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀውን የሜዳሊያ እና ገንዘብ ሽልማት ከክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተቀብለዋል፡፡ ተማሪዎቹን ያወያየችው የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት ዘጋቢ ሱመያ ሳሙኤል ናት ።

ሱመያ ሳሙኤል

ልደት አበበ