1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እንወያይ፤ ሰብዓዊ መብት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቶች ተግዳሮት በኢትዮጵያ

ፀሀይ ጫኔ
እሑድ፣ ሐምሌ 7 2016

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን በተለያዩ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በሌላ በኩል ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ እና ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚወተውቱ በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በስራቸው ሳቢያ ከመንግስት ጫና እና እንግልት እየጠነከረባቸው መምጣቱን እየገለፁ ነው።

https://p.dw.com/p/4iG1o
ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ እና ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚወተውቱ  በሰብዓዊ መብት  ላይ  የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በስራቸው ሳቢያ ከመንግስት ጫና እና እንግልት እየጠነከረባቸው መምጣቱን እየገለፁ ነው።
ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ እና ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚወተውቱ  በሰብዓዊ መብት  ላይ  የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በስራቸው ሳቢያ ከመንግስት ጫና እና እንግልት እየጠነከረባቸው መምጣቱን እየገለፁ ነው።ምስል Solomon Muchie/DW

እንወያይ፤ የሰብዓዊ መብት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን በተለያዩ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሰኔ 28 ቀን 2016  ዓ/ም ባወጣው  የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት፤  በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች ለማለት በሚያስችል ሁኔታ የዘፈቀደ እና የጅምላ እስር ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔ አለማክበር ተፈጽሟል።ኪነ-ጥበብ: “የጥበበኞቹ እስር እና መጉላላት አሳስቦናል”
 እንደ ሪፖርቱ  ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በታጣቂዎች  እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርስ የሞት እና የአካል ጉዳት መቀጠሉን እና በሕይወት የመኖር መብት አሳሳቢ መሆኑን አመልክቷል።ከሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በተጨማሪ ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ ያደረገ እገታ  ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑንም ሪፖርቱ  አሳስቧል።ኪነ-ጥበብ: “የጥበበኞቹ እስር እና መጉላላት አሳስቦናል”
በዚህ ሁኔታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አሳሳቢ በሆነባት ኢትዮጵያ ፤ ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ እና ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚወተውቱ  በሰብዓዊ መብት  ላይ  የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በስራቸው ሳቢያ ከመንግስት ጫና እና እንግልት እየጠነከረባቸው መምጣቱን እየገለፁ ነው።
በቅርቡ  የሰብዓዊ መብቶችን ዋና ትኩረት አድርገው የሚሰሩ 12 ሀገር በቀል  የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ በሀገሪቱ በሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ረገድ የሚታዩ ጉልህ ችግሮችን ነቅሰው በማውጣት  እና የእርምት እርምጃ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በመለየት ጠንካራ ውትወታ እንዳያደርጉ  ጫና እየተፈጠረባቸው መሆኑን  ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል
የሰብዓዊ ተማጋች ድርጅቶች ከመንግስት ጫና እየደረሰባቸው መሆኑን በጋራ መግለጫ ካወጡ 12 ሀገር በቀል  የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል አንዱ ነው።ምስል EHRDC

ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ የተባለው ማህበር የዘፈቀደ እስር እንዲቆም ጠየቀ
ከመንግስት በኩል ተደጋጋሚ ጥቃትና ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው እንደሚገኙ የገለጹት ድርጅቶቹ፤ይህም  ተስፋ ታይቶበት የነበረውን  የሲቪክ ምህዳር ዳግም ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መመለሱን አመላካች ነው ሲሉም ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በቅርቡ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ «የሰብዓዊ መብት የሚባል አዋጅ ተቋም አሠራርን መፈተሽ ያስፈልጋል»ብለዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ አያይዘውም «እኛ ደሞዝ የማንከፍለው ሌሎች ኃይሎች የቀጠሩት፣ ለሌሎች ኃይሎች ሪፖርት የሚያደርግ ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ከፈቀድን ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለእናነተ መተው ነው» ሲሉ ተደምጠዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡት መልስ
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች  ተግዳሮት  እንዴት ይገመገማል ? የዚህ ሳምንት እንወያይ ያነሳው ርዕሰ ጉዳይ ነው። በዚህ ርዕሰ ጉዳይ የመንግሥትን ሃሳብ ለማካተት በውይይት እንዲሳተፉ ለመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች እንዲሁም ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕረስ ሴክረተሪ በኢሜይል ግብዣ ልከን ነበር። ምላሽ ባለማግኘታችን ሃሳባቸውን ለማካተት አለመቻላችንን ማሳወቅ እንወዳለን።

በውይይቱ  የተሳተፉ እንግዶች፤

1,አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፤ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር 
2, ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የመብቶች እና ዴሞክራሲ ማዕከል ዳይሬክተር፤ በፈቃዱ ሀይሉ 
3, እንዲሁም አቶ መብርሂ ብርሃነ ፤የቅድሚያ ለሰብዓዊነት ኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር፤ ናቸው።

ሙሉ ውይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ፀሐይ ጫኔ