ኬንያ፤ ከአውሮጳ ህብረት ጋር የንግድ ስምምነት ተፈራረመች
ሰኞ፣ ሰኔ 12 2015ማስታወቂያ
ኬንያ ከአውሮጳ ህብረት ጋር የንግድ ስምምነት ተፈራረመች። ስምምነቱ ኬንያ የግብርና ምርቷን ወደ ትልቁ የኤክስፖርት ገበያ ከቀረጥ ነፃ እንድታስገባ የሚፈቅድም ነዉ። ይህ የአዉሮጳ ህብረት ከአፍሪቃ ጋር ጠንካራ የኢኮኖሚ ግንኙነት ስምምነት የመጣው ብራሰልስ ቻይናን ለመመከት ያደረገዉ ርምጃ ነዉ ተብሏል። የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በናይሮቢ ዛሬ በተካሄደው ከአዉሮጳ ህብረት ጋር የኢኮኖሚ ሽርክና ስምምነትን በይፋ እውቅና ሰጥተዋል። ሩቶ በሥነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ “ስምምነቱ ከንግድ ባለፈ ኢንቨስትመንቶችን እና ምርታማነትን ለማነቃቃት የተነደፈ ነው” ብለዋል።
የኬንያዉ የንግድ ሚኒስትር ሙሴ ኩሪያ ከአውሮጳ ህብረት የንግድ ኮሚሽነር ቫልዲስ ዶምብሮቭስኪ ጋር በመሆን ስምምነቱን ከተፈራረሙ በኋላ፡ "ዛሬ ኬንያ በጣም የምትኮራበት ቀን ነው፤ ለአውሮጳ ህብረትም በጣም የሚያኮራ ጊዜ ነው ብዬ አምናለሁ።" ሲሉ ተናግረዋል።
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ