ኬንያ ናይሮቢ የደረሰዉ ጥቃት
ሰኞ፣ መስከረም 13 2006
ካለፈው ቅዳሜ ቀትር ላይ ጀምሮ በእርግጥ የገበያ ማእከል ሳይሆን የጦር ሜዳ ሆኖ ነው የሰነበተው። ድንገት ወደማእከሉ ዘልቀው ከየኣቅጣጫው ተኩስ የከፈቱት በቅጡ የታጠቁ ኣሸባሪዎች በቁጥር ከ 15 እስከ 20 ይሆናሉ ተብለዋል እስከ ኣሁን በሮይተርስ ዘገባ መሰረት የሙዋቾች ቁጥር 70 ደርሰዋል የቆሰሉ ደግሞ ከ 200 በላይ ተቆጥረዋል የኬኒያ ፖሊስ እና የጦር ኃይሉ ከበባውን ኣጠናክሮ እና ወደ ውስጥ ዘልቆ በኣንድ በኩል በህይወት ያሉ ሰላማዊ ሰዎችን ለመታደግ እና ገዳዮችን ለመያዝ ኣሊያም ለመግደል የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆይተዋል ኣሁንም ድረስ ግን ኣላጠናቀቀም ምክኒያቱም ከጥቃቱ ለመደበቅ በላያቸው ላይ የዘጉትን ጨምሮ በተለያዩ ጉራንጉሮች የተደበቁም ስላሉ የኬኒያ የውስጥ ጉዳይ ካቢኔ ጸኃፊ ዮሴፍ ኦሌ ሌንቁ እንደሚሉት ወታደራዊው እርምጃ መካሄድ ያለበት በጥንቃቄ ነው።
የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ጥቃቱን ኣስመልክተው ለህዝባቸው ባሰሙት ንግግር ከዘግናን አረመኔያዊ ድርጊታቸው ጋር ተደብቀው ኣያመልጡም ኣይቀጡ ቅጣት እንቀጣቸዋለን ብለዋል
«የኬኒያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችም ኣስቸኩዋይ ስብሰባ ኣድርገውድርጊቱን ኮንነዋል በእንዲህ ኣይነቱ ጊዜ ኣሉ የቀድሞው የኬኒያ ጠ/ሚ ራይላ ኦዲንጋ የተቃዋሚ መሪዎችን በመወከል በእንዲህ ኣይነቱ ጊዜ በጋራ ሆነን በተቀናጀ መልኩ በሁኔታው ላይ መረባረብ ይኖርብናል»
«በከተማይቱ ናይሮቢ ዋና ዋና ሆስፒታሎች ያሉ ኃኪሞችም በጋራ ቁስለኖችን ለማትረፍ እየተረባረቡ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ ኬኒያውያንም የቁስለኖችን ህይወት ለመታደግ ደም ለመለገስ ተሰልፈዋል የሆስፒታል ምንጮች እንደሚሉት ደግሞ ቁስለኖቹ በኣብዛናው የቤተሰብ አባላት ናቸው ባል እና ሚስት እናት እና ልጆች ሌላም ሌላም ምክኒያቱም WEST GATE የገበያ ማእከል የናይሮቢ ሸማቾችም ሆኑ እንግዶች በግልም ሆነ በጋራ በተለይም ቅዳሜ እና እሁድ እየተዝናኑ ለመሸመት ጭምር የሚያዘወትሩበት ታዋቂ እና ምቹ የገበያ ማእከል ነው በእንዲህ ኣይነቱ ስፍራ ባልተጠበቀ ሳዓት የተቀነባበረ ተኩስ ቢከፈትም ቅዳሜ ከሳዓት በሁዋላ ከ 1000 በላይ ሰላማዊ ሰዎች በሰላም ከማእከሉ ለመውጣት ችለዋል ከውስጥ ያመለጡ የዓይን እማኖች እንደሚሉት ተኩዋሾቹ እስላም ባልሆኑ እና በተለይም በውጪ ሰዎች ላይ ያተኮሩ ነበሩ እስከ ኣሁን ትክክለናው ቁጥር ባይታወቅም ከሚዋቾቹ መካከል ሶስት ያህሉ የእንግሊዝ ዜጎች መሆናቸው ተሰምተዋል»
ኬኒያ ከኣልሸባብ ኣንጻር ስጋት ውስጥ የገባችው የዛሬ 2 ዓመት ወደዚያች ኣገር ግዛት ዘልቃ በቡድኑ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከጀመረች ወዲህ ነው በእርግጥ ያኔም ቢሆን ባለስልጣናቱ እንደሚሉት የኬኒያ ጦር ወደ ሶማሊያ የዘመተው ኣልሸባብ በኬኒያ ምድር የውጪ ጎብኒዎችን እና የእርዳታ ሰራተኖችን በማገት እና በመግደል የሚያደርሰውን የሽብር ጥቃት ለመበቀል ወይንም ለመከላከል ነበር።
የናይሮቢው ጥቃት እንደተሰማ የብሪታኒያ የውጪ ጉዳይ ሚ/ር ን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የመንግስታት መሪዎችም አድራጎቱን በእጅጉ ኮንነዉታል የኣሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም ትላንት እሁድ ለኬኒያው ኣቻቸው ኡሁሩ ኬኒያታ ስልክ ደውለው የኣልሸባብን ጥቃት ለመከላከል በተለይም እነዚህን ኣሸባሪዎች ለፍርድ ለማቅረብ ኣገራቸው ከኬኒያ ጎን እንደምትቆም ኣረጋግጠውላቸዋል
የኦጋዴን ነጻ ኣውጪ ግንባር ONLF ም በተለይ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ መግለጫ ኣውጥተዋል ለኬኒያ ህዝብ እና መንግስት በጉዳዩ ማዘኑን የገለጸው ONLF የሶማሌ ህዝብም በማንናውም መልኩ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ ኃይሎችን በማግለል ረገድ አቁዋም እንዲዪዝ ጥሪ ኣድርገዋል በኬኒያ የሚኖሩ የሶማሊያ ማህበረሰብ ኣባላትም በጉዳዩ ማዘናቸውን በመግለጽ የሽብር ተግባርን እያወገዙ መሆናቸው ተዘግበዋል።
«የታጠቁ አሸባሪዎች በቡድን ሆነው በናይሮቢ መናፈሻ አካባቢ ወደሚገነው WEST GATE የገበያ ማእከል በኃይል በመግባት በሰራተኖች እና ደንበኖች ላይ ትርጉም የለሽ ጥቃት ሰንዝረዋል እናም ብርካቶችን ገድለው ጥቂት የማይባሉትን ኣቁስለዋል እና እንደ መንግስት እና ኣገር ከሰለባዎቹ ቤተሰቦች ጋር እንቆማለን እያንዳንዱ ኬኒያዊ ከጎናቸው እንዲቆምእጠይቃለሁ እግዝኣብሄርም ከሀዘኑ መጽናናትን እንዲሰጣቸው እለምናለሁ ይህ ኣሳዛን ነገር ነው እንዲሁም በግል ምን እንደሚሰማችሁ ይገባናል በጣም የቅርብ ዘመድ የሆኑ የቤተሰብ አባላትን ኣታቸዋል።
የተወሰኑ ሰዎች ኣሁንም ድረስ እዚያው በህንጻው ውስጥ ይገናሉ የጸጥታ ኃይላችንም ከሁኔታው ጋር በመንቀሳቀስ ላይ ነው እነዚያን ኣሁንም ድረስ በአደጋ ውስጥ የሚገኑትን ዜጎች ለመታደግ ደግሞ መደራደርም ኣስፈላጊ ነው ቁጥሩም በእርግጥ ገና ኣልታወቀም የተወሰኑ ሰዎች በኣንደና ፎቅ እና በምድር ቤት ይገናሉ አሸባሪዎቹም እስከ ኣሁን እየተፈታተኑ ንው እንደሚታወቀው ሁንታው በጸጥታ ኃይላችን እጅ ተይዘዋል እርግጥ ሁኔታው በእነሱ እጅ እንዲቆይ እንፈልጋለን።
ጃፋር አሊ
ተክሌ የኋላ