1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ የአሁንና የቀድሞ ፕሬዝዳንቶችን የሚጠብቀው ሴክረት ሰርቪስ ሀላፊ ለምን ስራ ለቀቁ ?

ረቡዕ፣ ሐምሌ 17 2016

ባለፈው በቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ከተካሄደ የግድያ ሙከራ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸው በለቀቁት በቺትል ምትክ የመስሪያ ቤቱ ምክትል ሃላፊ ሮናልድ ሮዌ ለጊዜው በተጠባባቂነት የቺትል ስራ ተረክበዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትራምፕ ላይ ስለተፈጸመው የግድያ ሙከራ የሚካሄደው ምርመራ እንደቀጠለ ነው።

https://p.dw.com/p/4ih9a
USA Kimberly Cheatle Chefin Secret Service
ምስል Kevin Mohatt/REUTERS

የአሜሪካ የአሁንና የቀድሞ ፕሬዝዳንቶችን የሚጠብቀው ሴክረት ሰርቪስ ሀላፊ ለምን ስራ ለቀቁ ?

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትናንት ከሃላፊነታቸው በለቀቁት ፣Secret Service ተብሎ በሚጠራው መስሪያ ቤት ሃላፊ ኪምብርሊ ቺትል ምትክ በቅርቡ ሌላ ሰው እንደሚሾሙ ተናገሩ። ትራምፕ ላይ የተፈጸመው የግድያ ሙከራባይደን ለብዙ አስርት ዓመታት በመስኩ ያገለገሉትን ቺትልን በቆራጥነታቸው አወድሰው ሀገራችንን ለመጠበቅ ፣ሕይወታቸውን ለአደጋ ያጋለጡ ሰው ሲሉም አመስግነዋቸዋል። መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማቸውም ተመኝተውላቸዋል።

USA Butler Wahlkampf Trump Zwischenfall
ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላ ምስል Evan Vucci/AP Photos/picture alliance

 በቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ከተካሄደ የግድያ ሙከራ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸው በለቀቁት በቺትል ምትክ የመስሪያ ቤቱ ምክትል ሃላፊ ሮናልድ ሮዌ ለጊዜው በተጠባባቂነት ስራውን ተረክበዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትራምፕ ላይ ስለተፈጸመው የግድያ ሙከራ የሚካሄደው ምርመራ እንደቀጠለ ነው። በትራምፕ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራና ፖለቲካዊ አንደምታውቺትል ከሃላፊነታቸው ስለለቀቁባቸው ምክንያቶችና በግድያ ሙከራው ላይ የሚካሄደው ምርመራ ምን ላይ እንደደረሰ ከዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችንን ከአበበ ፈለቀ የተካሄደው ቀጣዩን ቃለ ምልልስ አድርገናል
አበበ ፈለቀ 
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ