ከጀርመን እንዲባረሩ ለተወሰነባቸው ስደተኞች ከለላ የምትሰጠው የጀርመን ቤተ ክርስቲያን
ረቡዕ፣ ጳጉሜን 1 2015የጀርመን ቤተ ክርስቲያን ጥበቃ ሽተው ወደ ርስዋ የሚመጡ ስደተኞችን ማስጠጋች ከጀመረች ባለፈው ሳምንት 40 ዓመታት ተቆጠሩ። በተለያዩ የጀርመን ከተሞች ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያን አንዳንዶቹ ስደተኞችን ማስጠጋት የጀመሩት የዛሬ 40 ዓመት በርዕሰ ከተማ በበርሊን በደረሰ አሳዛኛ አጋጣሚ መነሻ ነበር። በጎርጎሮሳዊው ነሐሴ 30፣ 1983 ዓ.ም. የሆነው ይህ አሳዛኝ ክስተት መላ ጀርመንን ነበር ያስደነገጠው። ተገን ጠያቂው ቲርካዊው ጀማል ከማል አልቱን በዚህ ቀን በበርሊኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። ፍርድ ቤቱ በእለቱ ስደተኛው ጀማል አምባገነን መንግሥት ወደነበራት ቱርክ ይባረር አይባረር የሚለውን ለመወሰን ነበር የተሰየመው። ጉዳዩን ለሁለተኛ ጊዜ ወደሚመለከተው ፍርድ ቤት አልቱንን ይዘው የመጡት የፖሊስ መኮንኖች እጁ የታሰረበትን ካቴና እንደፈቱለት ፍርድ ቤቱ ውስጥ ክፍት ወደነበረ መስኮት እየሮጠ ከሄደ በኋላ ዘሎ በመስኮቱ ወደቀ።አልቱን የወደቀው ከስድስተኛ ፎቅ ከ25 ሜትር ርቀት ላይ ነበር። ሕይወቱም ወዲያውኑ አለፈ። ፍርድ ቤቱ በርሊን ሀርድንቤርግ ሽትራሰ ላይ ነበር የሚገኘው። አሁን ግን በቦታው ሆቴልና አንድ የወይን መሸጫ ሱቅ ናቸው ያሉት። ሆኖም በዚህ ስፍራ በጎርጎሮሳዊው 1996 ፣ለአልቱን መታሰቢያ የቆመ ፣አራት ሜትር ርዝመት ያለው ሐውልት ይገኛል። በሐውልቱ ላይ « በፖለቲካ ምክንያት የተሳደዱ ሰዎች ተገን ማግኘት አለባቸው።» የሚል በጀርመንኛና በቱርክ ቋንቋ የተጻፈ መልዕክት ይገኛል። ከድንጋይ የተቀረጸው ይኽው ሐውልት በዚህ ዓይነት መንገድ ሕይወታቸውን ላጡ ስደተኞች መታሰቢያም ጭምር የተሰራ ነው።
በጀርመን የውጭ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃትና መከላከያውአልቱን ያኔ ሕይወቱን ያጠፋበት መንገድ መላ ጀርመንን በማስደንገጡ ትኩረት ይሳብ እንጂ እንባረራለን በሚል ስጋት ሕይወታቸውን ያጠፉ ስደተኞች ቁጥር ከ100 በላይ ይሆናል። የዛሬ 40 ዓመት አልቱን ከጀርመን እባረራለሁ በሚል ፍርሀት ሕይወቱን ካጠፋ በኋላ በጀርመን ጉዳዩ ማነጋገሩ ቀጠለ።በዚህ መሐል በርሊን የሚገኙ አንድ ካህን የበኩላችን መላ ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ።እኚህ ካህን ዩርገን ክዋንድት ይባላሉ ።በበርሊን ክሮይዝቤርግ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የጀርመን ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብን ከዛሬ 43 ዓመት አንስቶ በካህንነት ያገለግላሉ። አሁን የ79 ዓመት አዛውንት ናቸው። እርሳቸው የዚህ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በነበሩበት በዚህ ወቅት ከቱርክ ከሊባኖስ እና ከፍልስጤም ምድር የተሰደዱ የተለያዩ ሰዎች ማኅበረሰቡ እንዲረዳቸው ይጠይቁ ነበር። በዚህ የተነሳም እኛም ማኅበረ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ መሳተፍ ጀመርን ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። በ1983 በጸደይ ወቅት አንዳንዶቹ የአልቱን ጓደኞች በቤተ ክርስቲያኑ ማኅበረሰብ አዳራሽና በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የረሀብ አድማ መቱ።
ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ ከፍልስመጠጊያ ሰጣቸው። ይህ በሌሎች አገሮች ሲደረግ አይታይም። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ላለፉት 40 ዓመታት ስደተኞች የመባረር ስጋት ሲገጥማቸው ወይም አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ የጀርመን ዐብያተ ክርስቲያን ከለላ ይሰጣሉ። በፌደራል ደረጃ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠውን ከለላ የሚከታተል ቡድን እንደሚለው በዚህ ዓይነት መንገድ እርዳታ ያገኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ። በአሁኑ ጊዜ ከጎርጎሮሳዊው ነሐሴ አጋማሽ አንስቶ 655 የቤተሰብ አባላት የሚገኙባቸው 431 አባወራ ወይም እመወራ በቤተክርስቲያን ጥገኝነት አግኝተዋል።ከመካከላቸው 136ቱ ህጻናት ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ለስደተኞች ከለላ ከሚሰጠት አንዱ «የነጻው የወንጌላውያን የሉተራን ቤተ ክርስቲያን» ካህን ጎት ፍሪድ ማርትንስ ናቸው። ማርትንስ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በየቀኑ ተስፋ ያጡ ተገን ጠያቂዎች መልዕክት ይደርሳቸዋል። « ብዙ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች ዛሬም ያጋጥሙኛል። በየቀኑ ማለት ይቻላል ማኅበረሰባችን እንደ ቤተክርስቲያናችን ጥገኛ እንዲቀበላቸው የሚጠይቅ መልዕክት ይደርሰኛል።ይህ ደግሞ በዛም ሆነ በዚህ የኔ ውሳኔ አይደለም፤ የቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ነው የሚወስነው። ከአመልካቾች መሀል የሜርክል የ«አያቅተንም» የስደተኞች መርህ 5ኛ ዓመትመቀበል የምንችለው በጣም ጥቂት ፐርሰንቱን ነው። ብዙ የስራ ልምድ ያላቸው እንባረራለን ብለው እንደ ህጻን ልጅ ሲንቀጠቀጡ አያይቻለሁ።»
እርሳቸው እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ በበርሊን ሽቴግሊትዝ በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ምድር ቤት ውስጥ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ አንዳንድ ኢራናውያን ይገኛሉ። ከመካከላቸው አንዱ በምግብ ማብሰል የሰለጠነው ሰለሳሳን ሬዚ ነው። ከሰሜን ኢራን የመጣው ሬዚለዶቼቬለ እንደተናገረው ከሀገሩ የተሰደደው የቤተ ክርስቲያን አባል በመሆኑ ነበር። በስደት ላይ በቦስኒያና ክሮኤሽያ ድንበር ላይ እንደደረሰ ክፉና ተደብድቧል። ያለ ውሀና ያለዳቦም ብዙ ቀናት አሳልፏል። ክሮኤሽያ በሕገ ወጥ መንገድ የገባው ሬዚ ሁሌም « ከዚህ ሀገር ውጣ ነበር የሚባለው።»እዚያ እሞታለሁ ብሎ ይፈራ የነበረው ሬዚ ከብዙ መከራና ጭንቀት በኋላ በጀርመን የሽቴግሊትዙ ቤተ ክርስቲያን ጥገኝነት ካገኘ ከሁለት ቀናት በኋላ ነበር ጭንቀትና ፍርሀቱ የለቀቀው።ይህ ደግሞ ዳግም እንዲደርስበት አይፈልግም ።የ36 ዓመቱ ሬዚ አሁን በቤተክርስቲያኑ ምድር ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው። ጠዋት ብዙውን ጊዜ የሚያሳልፈው በስራ ነው። ከዚያ በኋላ ለርሱና ለሌሎች ከቄስ ማርትንስ ጋር ለሚኖሩ ስደተኞች ምግብ ያዘጋጃል። በአሁኑ ጊዜ ሬዚ ከዚህ ቤተ ክርስቲያን መውጣት አልተፈቀደለትም። ይህ ከጀርመን እንዲባረሩ ተወስኖባቸው ቤተክርስቲያን ጥገኝነት ሰጥታቸው እዚያ የሚኖሩ የበርካታ ሰዎች እጣ ፈንታ መሆኑን ማርተንስ ይናገራሉ።
«አንድ ሰው ፍርድ ቤት ማመልከቻውን ሳይቀበለው ቀርቶ ወደ ቤተክርስቲያን ለጥገኝነት ከመጣ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ እዚያው መቆየት አለበት። ይህም ችግር የሚያጋጥመው በጀርመን ብቻ ሳይሆን በሌሎች የአውሮጳ ሀገራትም ነው ።»ተችዎች እንደሚሉት በሕገ ወጥ መንገድ ክሮኤሽያን ወደ መሳሰሉ ሀገራት ለመግባት የሚሞክሩ ስደተኞች በነዚህ ሀገራት ትክክለኛው የተገን ጠያቂዎች አቀባበል አይደረግላቸውም።በዚህ የተነሳም ወደ ጀርመን ያቀናሉ። እስካሁን ይሰራበት በነበረው በአውሮጳ ኅብረት በተገን ጠያቂዎች ማመልከቻ አቀባበል የደብሊን ስምምነት መሠረት አንድ አመላካች መጀመሪያ በገባበት ሀገር ነው ማመልከቻው ውሳኔ ማግኘት ያለበት። በመሠረቱ ጀርመን እንደ ሬዚ ዓይነቶቹን ስደተኞች በሕጉ መሠረት መጀመሪያ ወደ ገቡበት የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገር ማባረር ትችላለች።ሬዚ አሁን ጀርመን ከገባ ስድስት ወራት ሆኖታል። መጤ ጠሉ አ.ኤፍ.ዴ የገዘፈበት ምርጫ
ቤተ ክርስቲያን የምታስጠጋቸውን ስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ቡድን እንደሚለው ቀደም ሲል ከተጠቀሱት 431 ተገን ፈላጊዎች 405ቱ ጉዳያቸው ከደብሊኑ ስምምነት ጋር የተያያዘ ነው።ለስደተኞች ከለላ መስጠት ፣ካህኑ ክዋንዲት እንደሚሉት የእምነታቸው መገለጫ ነው።ይህ ጉዳይም ባለፉት አርባ ዓመታት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲያነጋግር የዘለቀ ጉዳይ ነው። እርሳቸው እንደሚሉት የዛሬ አርባ ዓመት የነበረው አስተሳሰብና የአሁኑ ይለያል።የያኔው ሀሳብ ስደተኞች ወደ ሸሹበት ሀገር እንዳይመለሱ ነበር። አሁን ግን ጉዳዩ ስደተኞቹን ወደ ሌላ የአውሮጳ ኅብረት አባል ሀገር ተልልፈው እንዳይሰጡ ማድረግ ነው። በዚህ የተነሳም ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው ጥገኝነት አወዛጋቢ ሆኖ ዘልቋል።ፖለቲከኞች ሕጉ ችላ እየተባለ ነው ሲሉ እንደከሰሱ ነው። አንዳንዴ ካህናት ወይም የሃይማኖት መሪዎች ለዓመታት ፍርድ ቤት እየቀረቡ ተገን የሚሰጡበትን ምክንያት ማሳመን ይኖርባቸዋል።
በየዓመቱ ጀማል ከማል አልቱን የሚያስበው የበርሊኑ ሀገር አቀፉ የቤተ ክርስቲያን ለስደተኞች ከለላ አሰጣጥ ንቅናቄ ዘንድሮ አልቱን የሞተበትን 40ኛ ዓመቱን ዘክሯል።
የመጨረሻው አማራጭ ሕይወቱን በገዛ እጁ ማጥፋት የሆነበት የአልቱን መቃብር ከክሮይዝቤርግ ወጣ ብሎ በሚገኘው በበሊን ማሪንዶርፉ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይገናል። ዛሬ በሕይወት ቢኖሮ 63 ዓመት ይሆነው ነበር። መቃብሩ እስካሁን ድረስ በብዙዎች ይጎበኛል ።አሁንም አጠገቡ አበባ ጉንጉን ተቀምጦም ይታያል።
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ