እየተባባሰ የቀጠለዉ እስራኤልና የፍልስጤም ግጭት
ዓርብ፣ ግንቦት 6 2013ማስታወቂያ
ባለፈዉ ሰኞ በእስራኤል እና ፍልስጤም የተቀሰቀሰዉ ግጭት ወደለየለት ጦርነት እንዳያመራ ስጋት ቀስቅሶአል። ዓለማቀፉ ማህበረሰብ በእስራኤል እና ፍልስጤማውያን መካከል የሚካሄደዉ ውግያው እንዲረግብ ጥሪ እያስተላለፈ ነው። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሐማስ በእስራኤል ላይ እያደረሰ ነው ያሉትን የሮኬት ጥቃት ማዉገዛቸዉ ነዉ የተሰማዉ ። ባይደን እስራኤል የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት በመጠበቀ ራሷን የመከላከል መብት አላት ሲሉ መናገራቸዉ ተሰምቶአል። የእስራኤል እና የፍልስጤም ጦርነት ምን ሁኔታ ላይ ይገኛል ዛሬ። የእየሩሳሌሙን ወኪላችንን አነጋግረነዋል።
ዜናነህ መኮንን
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ