ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ
«በእሳት መካከል ነው ያለነው» ዜናነህ መኮንን
እሑድ፣ ሚያዝያ 6 2016ማስታወቂያ
እስራኤል ከኢራን ለደረሰባት መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ምን አይነት የአጸፋ ርምጃ እንደምትወስድ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ይሁንና ኢራን በበኩሏ እስራኤል ለደረሰባት ጥቃት የአጸፋ ርምጃ የምትወስድ ከሆነ የከፋ ርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስጠንቅቃለች።እስራኤል ለጋዛ ዕርዳታ እንዳይደርስ መከልከሏን እንድታቆም ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አዘዘ
ይህም ህዝቡን ስጋት ላይ ጥሏል። እስራኤል 99 በመቶ የተሰነዘረባትን ጥቃት ማክሸፍ ብትችልም ህዝቧ ከፍተኛ ድካም እና ጭንቀት ላይ ይገኛል። የእስራኤል ህዝብ አዳር ምን እንደሚመስል፤ እየሩሳሌም የሚገኘው የመካከላኛው ምስራቅ ዘጋቢያችን ዜናነህ መኮንን ሲገልፅ «በእሳት መካከል ነው ያለነው» ሲል ነው። ስለ ደረሰው ጉዳት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስተያየት ተከታዩን ብሎናል።
ዜናነህ መኮንን
ልደት አበበ