1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ የህብረቱን ጉባኤ ለማስተናገድ የሚያሳስብ ነገር የለም ፤ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር

ሐሙስ፣ ጥር 30 2016

የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ምለስ አለም ይህ የመጀመርያው የመሪዎች ስብሰባ አለመሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ "ለረጅም ጊዜ የአፍሪካ ሕብረትን በፈታኝ ወቅቶች" ማስተናገዷንና ምንም የሚያሳስብ ነገር እንደሌለ ለዚሁ ሥራ የተቋቃመው ብሔራዊ ኮሚቴ መግለፁን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4cAvb
Äthiopien | Botschafter Alem Meles
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ

ከየካቲት 6 እስከ 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ "ምንም የሚያሳስብ ነገር የለም" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለቀረበለት የፀጥታና ድኅንነት ዝግጅት ምላሽ ሰጠ። 

የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ምለስ አለም ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ አካባቢ ታጣቂዎች ከመንግሥት ጋር የትጥቅ ግጭት በሚያካሂዱበት በዚህ ወቅት ምን ያህል ለጉባኤው ተዘጋጅታለች በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ይህ የመጀመርያው የመሪዎች ስብሰባ አለመሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ "ለረጅም ጊዜ የአፍሪካ ሕብረትን በፈታኝ ወቅቶች" ማስተናገዷንና ምንም የሚያሳስብ ነገር እንደሌለ ለዚሁ ሥራ የተቋቃመው ብሔራዊ ኮሚቴ መግለፁን ተናግረዋል። «ያለ ፈተና የፀና ሕልውና የለም» - የኢትዮጵያ የውጭ ገዳይ ሚኒስቴር
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የፈረመችውን የመግባቢያ ስምምነት ትከትሎ የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት ውጥረት ውስጥ እየገባ ምርጫ ሆኑ ተጠቅሶ በማሳያነት ሰሞኑን በደቡብ ሶማሊያ ለተሃዎ በተባለ ስፍራ ስድስት ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን በተመለከተ የመንግሥትን አቋም እንዲገልፁ የተጠየቁት አምባሳደር መለስ አለም ድርጊቱ በአልሸባብ መፈፀሙን ገልፀው "ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እየሞከርን ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።//

አሕጉራዊ ጉባኤ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ያደረገችው የፀጥታ ዝግጅት 

Äthiopien 60. Jahrestag der Afrikanische Union (AU)
ምስል Solomon Muchie/DW

አፍሪካ በ2021 የጥይት ድምፅ የማይሰማበት ክፍለ ዓለም እንዲሆን አደርጋለሁ ሲል የተለጠጠ እቅድ አስቀምጦ የነበረው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎቹ አዲስ አበባ ላይ በየዓመቱ ቢሰባሰቡም ከኢትዮጵያ እስከ ሱዳን ታጣቂዎች ከመንግሥት ከመዋጋት፣ በምዕራብ የአሕጉሩ ዳርቻ የመንግሥት ፍንቀላ ወይም ሰዒረ መንግሥታት ጎልተው ከመታየት የሚታደግ የፖለቲካ መፍትሔ ማስቀመጥ የቻለ አይመስልም።

የሕብረቱ መቀመጫ የሆነችው የጉባኤ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ በቀጣዩ ሳምንት ለሚጀምረው 37 ኛው የመሪዎች ጉባኤ እስካሁን የ34 ሀገራት መሪዎች በጉባኤው እንደሚሳተፈ ማረጋገጫ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ዛሬ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ታጣቂዎች ከመንግሥት ጋር በተለያየ ቦታ የትጥቅ ግጭት በሚያደርጉባት ኢትዮጵያ መንግሥት ለዚህ ጉባኤ ምን ያህል የፀጥታ እና የደኅንነት ሥራ አከናውኗል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።የመንግሥት እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ድርድር እንደቀጠለ መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ
"ምንም የሚያሳስብ ነገር የለም" ብለዋል። 

ሰሞኑን በሶማሊያ ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የፈረመችውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት ውጥረት ውስጥ እየገባ  መሆኑ ተጠቅሶ በማሳያነት ሰሞኑን በደቡብ ሶማሊያ ለተሃዎ በተባለ ሥፍራ ስድስት ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን በተመለከተ የመንግሥትን አቋም እንዲገልፁ የተጠየቁት አምባሳደር መለስ አለም ድርጊቱ በአልሸባብ መፈፀሙን ገልፀው "ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እየሞከርን ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቃል ዐቀባዩ ምላሽ ያልሰጡባቸው የጋዜጠኞች ጥያቄዎች

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ከተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ጋር በተያያዘ ለጎረቤት ሀገራት ማብራሪያ መስጠት እንደምትፈልግ ለኢጋድ ያቀረበችው ጥያቄ ምላሽ ምን እንደሆን የተጠየቁት ቃል ዐቀባዩ ምላሽ አልሰጡበትም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተባበሩት መንግሥታት ባለስልጣን ስለ ኢትዮጵያ ያወጡትን መግለጫ አጣጣለ

ከዚህ በፊት በሳውዲ አረቢያ እና በየመን ድንበር ላይ ስለተገደሉ ኢትዮጵያዊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እያጣራ መሆኑን ግልጾ የነበረ ቢሆንም ምን ላይ ደረሰ በሚል ለቀረበ ጥያቄም ምላሽ አልሰጡበትም። በተመሳሳይ በአማራ ክልል የተራዘመውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ገዳዩ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን መግለፃቸው  ተገልጾ የመንግሥትን አቋም እንዲገልፁ የተጠየቁት ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ዐዋጁን የሚመለከተው አካል እንጅ ውጭ ጉዳይ ምላሽ እንደማይሰጥ ተናግረዋዋ።

ኢትዮጵያ ከኬንያ እስከ ኤርትራ ፣ ከሶማሊያ እስከ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን እንዲሁም በሌሎች የምትዋስንባቸው ሀገራት ሉዓላዊ የግዛት ወሰኗ እና ድንበሮቿ ምን ያህል የተከበሩ ናቸው?  አሁንም በኢትዮጵያ ድንበር ላይ ዘልቀው በመግባት ችግር የሚፈጥሩ የሌላ ሀገር የፀጥታ ኃይላት ስለመኖራቸው ቅሬታ መኖሩ ተጠቅሶ የተጠየቁት አምባሳደር መለስ አለም "በውይይት እና በመነጋገር ይፈታል" ከማለት በቀር ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ