1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ውስጥ የተዘነጋው ጦርነት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 10 2015

ጀርመን ውስጥ ታዋቂ የሆነው ጸሓፊና ጋዜጠኛ ናቪድ ኪማኒ ሰሞኑን ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ወደ ጀርመን ተመልሷል ። ጋዜጠኛው ከጉዞው መልስ ዶይችላንድ ፉንክ ከተሰኘው የሬዲዮ ጣቢያ ጋር በጀርመንኛ ቋንቋ ቃለ መጠይቅ አድርጓል ።

https://p.dw.com/p/4QG4G
Navid Kermani | deutsch-iranischer Schriftsteller
ምስል Christoph Hardt/Panama Pictures/picture alliance

«በሴቶች ላይ የተፈጸመው በደል እጅግ አሳዛኝ ነው»

ጀርመን ውስጥ ታዋቂ የሆነው ጸሓፊና ጋዜጠኛ ናቪድ ኬርማኒ ሰሞኑን ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ወደ ጀርመን ተመልሷል ። ጋዜጠኛው ከጉዞው መልስ ዶይችላንድ ፉንክ ከተሰኘው የሬዲዮ ጣቢያ ጋር በጀርመንኛ ቋንቋ ቃለ መጠይቅ አድርጓል ። ስለ ትግራይ እና አማራ ክልል ቆይታው በተመለከተ ከሬዲዮ ጣቢያው ጋር ባደረገው አጠር ያለ ቃለ መጠይቅ፦ «ኢትዮጵያ ውስጥ የተዘነጋ» ባለው ጦርነት ስልታዊ በሆነ መልኩ የሰብአዊ መብቶች መጣሳቸውን ገልጧል ። በተለይ ደግሞ ሴቶች ላይ የደረሱ በደሎች ከአእምሮው እንደማይወጣም ተናግሯል ። «የዩክሬን ጦርነትን አሳንሼ ባልመለከተውም በዩክሬን ጦርነት የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸመው በደል መዘንጋቱ ያሳዝናልም» ብሏል ። የቤርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ቃለ መጠይቁን እንደሚከተለው አሰናድቷል ። 

ቀጣዩ ዘገባ የተለያዩ መጻሕፍትንና በርካታ ጽሑፎችን ፣ ጀርመን አገር በየጊዜው ስለሚያቀርበው ታዋቂው ጸሓፊ እና ጋዜጠኛ ናቪድ ኪማኒ ነው ። ሰውዬው በተለያዩ ጊዜያቶች የተለያዩ አካባቢዎችን ብድግ ብሎ የሚጎበኝ ነው ። ጽሑፎቹንና ዘገባዎቹን በሳምንታዊው የ«በዜጦች አምድ» መሰናዶዋችን ላይ አልፎ አልፎ -ለማስታወስ -አቅርበንላችሁም ነበር ።

ሰሞኑን በጋዜጠኛነት ሥራ ሳይሆን በሀገር ጎብንነት፤ በመንገደኛ ደረጃ ፣ወደዚያ ወርዶ በዓይኑ ያየውንና እዚያ የተመለከተውን ነገር፣ ለአንድ «ዶችላንድ ፉንክ» ለተሰኘ ጀርመን አገር ውስጥ ለታወቀ የራዲዮ ጣቢያ ሰሞኑን አስተያየቱን ሰጥቶአል ።

በትውልዱ ኢራናዊ በዜግነቱ ጀርመን የሆነው ጸሓፊ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ደርሶ «የትግራይ እና የአማራ ክልሎች» የሚባሉትን አካባቢዎች  ተመልክቶ ተመልሷል ። ናቪድ ካርማኒ ይባላል ።
«ተቻችሎ እና ተከባብሮ በአንድነት መኖር» የሚለው፣ የልዑል ዶክተር አስፋ ወሰን አሥራተ መጽሓፍ ውስጥ አንደኛውን ምዕራፍ ከአበረከቱት ጸሓፊዎች ውስጥም ናቪድ ካርማኒ ይገኝበታል ።

ደስ ሲለው እቤቱ ተቀምጦ መጽሓፍ ጽፎ ያወጣል ። ሲመቸው እንደ መንገደኛ ጋዜጠኛ ተዘዋውሮ አስገራሚና አስደናቂ ታሪኮችን ከመንገድ ላይ ሰብስቦ ለአንባቢዎቹ ያቀርባል ። ዩክሬን ነበር ። ሶሪያ ሄዷል ። ማደጋስከርም ደርሶ እዚያ ያውንና እዚያ የተመለከተውን እንድናነበውም አድርጓል ።

ዳቪድ ኬርማኒ / ይልማ ኃይለሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ