1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሰመጉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የ 2022 ዓ.ም ተሸላሚ ሆነ

ሰኞ፣ ግንቦት 22 2014

መንግሥታዊ ያልሆነው የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ኢሰመጉ የያዝነው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2022 የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰብዓዊ መብቶች ሽልማት ተሸለመ። ኢሰመጉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመብቶች ተከራካሪ ከሆነው ከጀርመኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ነው ላበረከተው አስተዋጽኦ ሽልማት ያገኘው።

https://p.dw.com/p/4C3af
Logo des Ethiopian Human Rights Council
ምስል Ethiopian Human Rights Council

«ሽልማቱን ዛሬ በርሊን ላይ ተረክቧል»

ለሦስት አስርት ዓመታት ገደማ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይፋ በማድረግ ቆይቷል፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ። በጎርጎሪዮሳዊው 1991 የተመሠረተው ኢሰመጉ አሁን በመላ ሀገሪቱ ዘጠኝ የሚሆኑ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አሉት።  መንግሥታዊ ያልሆነው የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ ሀገራዊ ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የመብቶች ተከራካሪ ከሆነው ከጀርመኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ላበረከተው አስተዋጽኦ የ2022 የሰብዓዊ መብቶች ሽልማት ተበርክቶለታል። ሽልማቱን የኢሰመጉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳን ይርጋ በዛሬው ዕለት በጀርመኗ ዋና  ከተማ በርሊን ላይ በተካሄደው ሥርነስርዓት ላይ ተረክበዋል። አቶ ዳንን ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ በስልክ አነጋግረናቸዋል።

Logo von Amnesty International

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ