አፍሪቃ ፣ አይሲሲ እና የአፍሪቃ ህብረት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 17 2009ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር ድላማኒ ዙማ አባል ሀገራት የፍትህ ስርዓታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠየቁ ። ዙማ ሦስት የአፍሪቃ ሀገራት ከዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት በምህጻሩ አይ.ሲ.ሲ ለመውጣት ስለመወሰናቸው በሰጡት አስተያየት የድርጅቱ አባል መሆንም ሆነ ከአባልነት መውጣት የየሀገራቱ ሉዓላዊ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል ። አፍሪቃውያን በራሳቸው ፍርድ ቤት የሚዳኙበትን ስርዓት መጠናከር እንደሚገባቸውም አሳስበዋል ። ደቡብ አፍሪቃ እና ብሩንዲ ባለፈው ሳምንት እንዲሁም ጋምብያ ደግሞ ከትናንት በስተያ ከአይሲሲ ለመውጣት መወሰናቸውን አስታውቀዋል ። የደቡብ አፍሪቃው ወኪላችን ዘገባ አለው ።
መላኩ አየለ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ