አዲሱ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ
ሐሙስ፣ ግንቦት 25 2014ማስታወቂያ
አሜሪካ ለአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና አዲስ ልዩ መልዕክተኛ መሾሟ በአካባቢው ያለው የሰላምና መረጋጋት ቀውስ በዘላቂነት ያለመፈታቱ እንዲሁም የሚመደቡት ባለሥልጣናትም ችግሩን ለመፍታት አቅም እንዳነሳቸው ማሳያ መሆኑን አንድ የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ተናገሩ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲሱን ሹመት በተመለከተ ሲናገሩ በአካባቢው ለምናደርገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ቁርጠኛ መሆናችንን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
የፖለቲካ ቀውስ፣ የሽብር ጥቃት፣ የፀጥታ መደፍረስ፣ ረሐብና ስደት መገለጫው በሆነው የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ የአሜሪካ ፍላጎትና ፖሊሲ በግለሰቦች መለዋወጥ የማይቀየር መሆኑን ያነጋገርናቸው ባለሞያ ገልፀዋል።
በአንድ ዓመት ገደማ ጊዜ ውስጥ ሦስተኛ ሰው ሆነው ሹመት የተቀበሉትን ልዩ መልእክተኛ አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ