1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢዉ የጋዜጠኞች እስርና የሃሳብ ነጻነት መደፍለቅ በኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2015

ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ተግባራዊ እንዲሆን የፍትሕ ሥርዓቱ በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ ድንጋጌ ሊመራ ይገባል›› ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት አስታወቀ። ምክርቤቱ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ተግባራዊ እንዲሆን የፍትሕ ሥርዓቱ በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ ድንጋጌ መሰረት ሊመራ ይገባል ሲል አሳስቧል።

https://p.dw.com/p/4QCP4
Social Media Apps auf Smartphone
ምስል picture alliance / empics

የታሰሩ ጋዜጠኞችና ትችት አቅራቢዎች በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል

ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ተግባራዊ እንዲሆን የፍትሕ ሥርዓቱ በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ ድንጋጌ ሊመራ ይገባል›› ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት አስታውቆዋል።  ዛሪ  ረፋዱን ምክርቤቱ ባውጣው መግለጫ  ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ተግባራዊ እንዲሆን የፍትሕ ሥርዓቱ በመገናኛ ብዙሃን አዋጁ ድንጋጌ መሰረት ሊመራ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት አሳስቧል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መገናኛ ባለስልጣን እኔ ህጋዊ እውቅና ሰጥቼው ከሚሰራ ተቁዋም ውስጥ የታሰረ  ጋዜጠኛ የለም ሲል ይናገራል ።

የኢትዮጵያ መንግስት የግል ጋዜጠኞችን፣ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ አሰራጮችን፣ተቺዎችንና የፖለቲካ አቀንቃኞችን ማሰሩን እንደቀጠለ ባለፈዉ ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት በሳምንቱ መገባደጃ ይፋ ባደረገዉ መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች ባለፉት ሁለት ሳምንት ዉስጥ ቢያንስ ስምንት  ጋዜጠኞችን ጨምሮ ፣የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ሰራተኞችና የፖለቲካ ተቺዎችን ማሰራቸዉን ማስታወቁ ይታወሳል።  

ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ተግባራዊ እንዲሆን የፍትሕ ሥርዓቱ በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ ድንጋጌ ሊመራ ይገባል›› ሲል ያሳሰበው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ከሕግ አግባብ ውጪ ተይዘው ፤ታፍነውና  ያለፍርድ ቤት ተዛዝ ይታሰራሉ በሚዲያ ተቁዋማቱ ላይም ህጋዊ ያልሆነ  ብርበራ  በተደጋጋሚ  በመንግስት ሀይል መፈፀሙ አሳስቦኛል ሲል  መግላጫ ሰጥቶዋል የምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምራት ሀይሉ ለ DW እንድተናገሩት ። የዚህ አይነቱ ደርጊት መደጋጋም እና ከጊዚ ወደጊዚ መበራከት ተገቢውን ምላሽ  እና መሻሻል ካላገኛ   በሙያው ላይ የሚፈጥረው ተጸኖ ከፍተኛ ነው።

በሚዲያ አማካኝነት ተፈጽሟል በተባለ ወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑ ጋዜጠኞች በፖሊስ ሲያዙ ብቻ ሳይሆን ፍርድ ቤት ሲቀርቡም በአዋጁ መሠረት ያለመፈፅሙ ባለሙያዎች ሥራቸውን በነጻነት እንዳይሰሩ፣ እንዲሸማቀቁና   ከማድረጉም በላይ በሀገራችን የፕሬስ ምህዳሩ ያጠበዋል ሲሉ አቶ ታምራት ሀይሉ  ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን  ከጋዜጠኛው ጋር ያለው ኝኙነት የሚጀምረው ጋዚጠኛው ከሚሰራበት ተቁዋም  ነው ። በ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ፍቃድ አግኝቶ ከሚሰራ ተቁዋም ውስጥ የታሰረ ጋዚጠኛ ስለመኖሩ እስካሁን የሰማነው የለም ሲሉ ለ DW የተናገሩት የመገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት  አቶ ደሴ ከፍአለ።

ሀና ደምሴ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ