1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት አል ነጃሺ መስጊድ ጥገና መጀመሩ

ዓርብ፣ ጥቅምት 15 2017

በሰሜኑ ጦርነቱ ወቅት ከባድ ጉዳት የደረሰበት በትግራይ ክልል የሚገኘው ጥንታዊው አል ነጃሺ መስጊድ፥ በቱርክ መንግሥት ድጋፍ ጥገና እየተደረገለት ነው። አንድ ወር ባስቆጠረው የቅርሱ ጥገና ሥራ የተሰማሩ ባለሙያዎች በስምንት ወራት ውስጥ የመስጊዱን የቀድሞ ይዞታ ለመመለስ እየሠሩ መሆኑን ይገልፃሉ።

https://p.dw.com/p/4mF3X
አል ነጃሺ መስጊድ
ጥገና ላይ የሚገኘው አል ነጃሽ መስጊድ ምስል Million Hailesilassie/DW

አል ነጃሺ መስጊድ ጥገና

በጦርነቱ ወቅት ከባድ ጉዳት የደረሰበት በትግራይ ክልል የሚገኘው ጥንታዊው አል ነጃሺ መስጊድ፥ በቱርክ መንግሥት ድጋፍ ጥገና እየተደረገለት ነው። በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጅማሮ በ2013 ዓመተ ምሕረት ኅዳር ወር ከፍተኛ ጉዳትን እና ዝርፍያ የደረሰበት ይህ ጥንታዊ የእስልምና ሃይማኖት ቅርስ፥ ጥገናው ከተጀመረ አንድ ወር ሆኖታል። በቅርሱ ጥገና የተሰማሩ ባለሙያዎች በስምንት ወራት ውስጥ የመስጊዱንየቀድሞ ይዞታ ለመመለስ እየሠሩ መሆኑን ይገልፃሉ።

የመቀሌው ዘጋቢያችን ሚሊየን ኃይለሥላሴ ወደ ቦታው ተጉዞ ተከታዩን አዘጋጅቷል።

ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ