1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የናይጀሪያውን ተገን ጠያቂዎች እጣ ፈንታ በጀርመን

ሰኞ፣ ኅዳር 3 2016

ከጎርጎሮሳዊው ጥር 2023 እስከ መስከረም ድረስ ከ1800 በላይ ናይጀሪያውያን ጀርመን ውስጥ ተገን እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የሕግ ባለሞያዋ ናይጀሪያዊቷ ጁዲት ኢቢ እንደሚሉት በርካታ ናይጀሪያውያን ከሀገራቸው የሚወጡት በጀርመን የተሻለ የስራ እድልና የኑሮ ደረጃ ፍለጋ ነው።የሚሰደዱትም መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ መብቶቻቸውን ባለሟሟላቱ ነው ይላሉ ።

https://p.dw.com/p/4Yje9
Spanien Flüchtlinge aus Afrika kommen in Arguineguin an
ምስል Borja Suarez/REUTERS

የናይጀሪያውን ተገን ጠያቂዎች እጣ ፈንታ በጀርመን

ወደ አውሮጳ የሚካሄድ ፍልሰት ናይጀሪያ ውስጥ ሞቅ ያለ ክርክር አስነስቷል። ጉዳዩ ትኩረት ያገኘው በተለይ ጀርመን ማመልክቻቸው ተቀባይነት ያላገኘ ተገን ጠያቂዎችን በቀላሉ ልታባርር የምትችልበትን እቅድ ይፋ ካደረገች በኋላ ነው። እቅዱ ምናልባትም ቁጥራቸው ወደ 12 ሺህ ሊደርስ የሚችል ጀርመን የሚገኙ ናይጀሪያውያን ተገን ጠያቂዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሊያደርግ ይችላል እየተባለ ነው። ምንም እንኳን በርሊን የፍልሰት ፖሊሲዋን ለማጠናከር ብትወስንም በርካታ ናይጀሪያውያን ግን አሁንም አውሮጳ ለመኖር ማለማቸውን አላቆሙም። 


«ለተሻለ የስራ እድል ጀርመን ለመሄድ እፈልጋለሁ ።አንዳንዶች እዚያ ሄደው በአጓጉል ስራ ቢሰማሩም ሌሎች ይህን ያደርጋሉ ማለት አይደለም። ይህን የምትለው አንዲት የአቡጃ ነዋሪ ናት።  ይህ የአቡጃ ነዋሪም ተመሳሳይ ፍላጎት አለው። «እዚህ ችግሩ እየከበደ ስለመጣ በሕጋዊ መንገድ የመሄድ እድል ባገኝ ለኔ የተሻለ ነው። መከራው ጠንቶብናል »
አንዳንድ ናይጀሪያውያን ግን ወደ አውሮጳ የሚካሄድ ፍልሰትን አይቀበሉም። «አንዳንድ ሰዎች ያለዓላማ ነው የሚሄዱት። ዓላማ ሊኖርህ ይገባል። ለምንድነው እዚያ የምትሄደው? የጀርመንን ጉዳይ በተመለከተ መመለሱ ቀጣዩ ተግባር ነው? እኔ በመጀመሪያ ደረጃ ናይጀሪያን ለቅቄ መሄድ አልፈልግም ።ናይጀሪያዊ ሁሉ ሀገሪቱን ለቆ ከሄደ ናይጀሪያውያን ተብለው የሚጠሩ እነማን ሊገኙ ነው? ናይጀሪያን ለቆ ከመውጣት ይልቅ ልንገነባት ይገባል። »

የጀርመን የህዝብተወካዮች ምክርቤት ባለፈው ሰኔ አዲስ የፍልሰት ሕግ ማሻሻያ አጽድቋል። ማሻሻያው የተዘጋጀው ከአውሮፓኅብረት አባል ሀገራት ውጭ ከሆኑ አገርት ተጨማሪ ተፈላጊ ባለሞያዎች ወደሀገሪቱ እንዲመጡ ማበረታታት ነው። 
ጀርመን ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን በፍጥነት ለማባረር  እያቀደች በሌላ በኩል ደግሞ  በስራ ገበያው ውስጥ የተፈጠረውን ክፍተት እንዲሞሉ ተጨማሪ የውጭ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለመሳብ ትፈልጋለች። የጀርመን የህዝብተወካዮች ምክርቤት ባለፈው ሰኔ አዲስ የፍልሰት ሕግ ማሻሻያ አጽድቋል። ማሻሻያው የተዘጋጀው ከአውሮፓኅብረት አባል ሀገራት ውጭ ከሆኑ አገርት ተጨማሪ ተፈላጊ ባለሞያዎች ወደሀገሪቱ እንዲመጡ ማበረታታት ነው። ምስል Europa Press/ABACA/picture alliance

ለምንድን ነው በርካታ ናይጀሪያውያን ጀርመን መኖር የሚፈልጉት ?

ከአፍሪቃ በህዝብ ብዛት አንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውና ከምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት የተረጋጋ ዴሞክራሲ አላት የምትባለው ናይጀሪያ ከሙስና፣ ከስራ አጥነት እና በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል 14 ዓመታት ያስቆጠረ ግጭት ከሚያካሂዱ አክራሪ ሙስሊሞች ጋር እየታገለች ነው። በግጭቱ ከጎርጎሮሳዊው 2009 ዓም አንስቶ 40 ሺህ የተገመቱ ሰዎች ሲገደሉ  ሁለት ሚሊዮን ደግሞ ተፈናቅለዋል። በዚህ ዓመት ከጎርጎሮሳዊው ጥር 2023 እስከ መስከረም ወር ድረስ ከ1800 በላይ ናይጀሪያውያን የጀርመን መንግሥት ተገን እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የሕግ ባለሞያዋ ናይጀሪያዊቷ ጁዲት ኢቢ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ በርካታ ናይጀሪያውያን ሀገራቸውን ጥለው የሚወጡት በጀርመን የተሻለ የስራ እድል ፣ከፍተኛ ክፍያ እና የተሻለ የኑሮ ደረጃ ፍለጋ ነው። ናይጀሪያውያን ከሀገራቸው የሚሰደዱት መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ መብቶቻቸውን ባለሟሟላቱ ነው ይላሉ ። የወሲብ ንግድ በአውሮጳ


«በዚህ ሁኔታ ስራዎቹን ባለማከናወንና ፖሊሲዎቹን ባለመተግበር የናይጀሪያን መንግሥት እወቅሳለሁ። የናይጀሪያ ፌደራል ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ፣ምዕራፍ ሁለት የዜጎችን ሕይወት የሚያመቻቹ ፣ናይጀሪያ ውስጥ ዜጎች ቀላል ሕይወት እንዲመሩ የሚያስችሉ ማኅበራዊ ፖሊሲዎችን አካቷል። ሆኖም መንግሥት እነዚህን አገልግሎቶች መስጠት አለመቻሉ ነው ዋናው ችግር።»
በጎርጎሮሳውያኑ ጥቅምት መጨረሻ ናይጀሪያን የጎበኙት የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ወደ ጀርመን የሚደረግ ፍልሰትን ለማስተዳደር ለናይጀሪያ መንግሥት የቅርብ አጋርነት ጥሪ አድርገው ነበር ። ሾልዝ ከጀርመንና ከሌሎች ሀገራት የሚጋዙ ፣ማመልከቻቸው ተቀባይነት ያላገኘ ተገን ጠያቂዎችን ለመደገፍ የተቋቋሙ የፍልሰት ማዕከላት እንዲስፋፉ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።ተቀባይነት ያላገኙ ተገን ጠያቂዎች እንዲባረሩም አጽንኦት የሰጡት ሾልዝ ይህ ከሁለቱም ወገን በኩል ዝግጅትና ውረታ እንደሚፈልግም ተናግረዋል።

እቅዱ ምናልባትም ቁጥራቸው ወደ 12 ሺህ ሊደርስ የሚችል ጀርመን የሚገኙ ናይጀሪያውያን ተገን ጠያቂዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሊያደርግ ይችላል እየተባለ ነው። ምንም እንኳን በርሊን የፍልሰት ፖሊሲዋን ለማጠናከር ብትወስንም በርካታ ናይጀሪያውያን ግን አሁንም አውሮጳ ለመኖር ማለማቸውን አላቆሙም። 
ወደ አውሮጳ የሚካሄድ ፍልሰት ናይጀሪያ ውስጥ ሞቅ ያለ ክርክር አስነስቷል። ጉዳዩ ትኩረት ያገኘው በተለይ ጀርመን ማመልክቻቸው ተቀባይነት ያላገኘ ተገን ጠያቂዎችን በቀላሉ ልታባርር የምትችልበትን እቅድ ይፋ ካደረገች በኋላ ነው። ምስል Tim Brakemeier/dpa/picture alliance

የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲንቡ በበኩላቸው ተመላሾቹን ለመቀበል ሀገራቸው ፈቃደኛ መሆንዋንና እና የፍልሰት ማዕከላትን ለማስፋፋት እቅዱ በሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።ቲኑቡ የሚመለሱት ናይጀሪያውያን እስከሆኑ ድረስ መምጣታቸውን እደግፋለሁ ብለዋል።ሆኖም ማንነታቸውን ማረጋገጡ ግን ከባድ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።ከጀርመን መባረር አለባቸው ከተባሉት 14 ሺህ የሚጠጉ ተገን ጠያቂዎች፣ ወደ 12,500 የሚሆኑት ጀርመን መቆየት የቻሉት በአመዛኙ ማንነታቸውን የሚገልጹ ሰነዶች ስለሌላቸው ነው።
ሴሊስቲን ኦዶጉ በአቡጃ ዩኒቨርስቲ የማኅበራዊ ጉዳዮች ጥናት መምህር ናቸው። ጀርመን በሀገርዋ የመቆየት መብት የሌላቸውን ናይጀሪያውያንን ለመመለስ መወሰኗን አጥብቀው ይደግፋሉ።
የናይጀሪያ ፕሬዚደንት እና ፀረ ሙሰና ዘመቻቸው« ናይጀሪያውያን ምንም በማይሰሩበት ሁኔታ ጀርመን ውስጥ መቆየታቸው ያሳዝናል።ሆኖም የጀርመን ባለሥልጣናት እንዲባረሩ የሚጠይቁት ኤኮኖሚያቸውን ለመጠበቅ ነው። ይህ ደግሞ ማንኛውም ሃላፊነት የሚሰማው መንግሥት የሚያደርገው ነው። ሕገ ወጥ ስደተኞች ኅብረተሰቡ መሀል ከተገኙ ችግር ይፈጥራሉ።»

በግጭቱ ከጎርጎሮሳዊው 2009 ዓም አንስቶ 40 ሺህ የተገመቱ ሰዎች ሲገደሉ  ሁለት ሚሊዮን ደግሞ ተፈናቅለዋል። በዚህ ዓመት ከጎርጎሮሳዊው ጥር 2023 እስከ መስከረም ወር ድረስ ከ1800 በላይ ናይጀሪያውያን የጀርመን መንግሥት ተገን እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ከአፍሪቃ በህዝብ ብዛት አንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውና ከምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት የተረጋጋ ዴሞክራሲ አላት የምትባለው ናይጀሪያ ከሙስና፣ ከስራ አጥነት እና በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል 14 ዓመታት ያስቆጠረ ግጭት ከሚያካሂዱ አክራሪ ሙስሊሞች ጋር እየታገለች ነው። ምስል Europa Press/ABACA/picture alliance

ጀርመን የሰለጠነ የሰው ኃይል ትፈልጋለች 

ጀርመን ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን በፍጥነት ለማባረር  እያቀደች በሌላ በኩል ደግሞ  በስራ ገበያው ውስጥ የተፈጠረውን ክፍተት እንዲሞሉ ተጨማሪ የውጭ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለመሳብ ትፈልጋለች። የጀርመን የህዝብተወካዮች ምክርቤት ባለፈው ሰኔ አዲስ የፍልሰት ሕግ ማሻሻያ አጽድቋል። ማሻሻያው የተዘጋጀው ከአውሮፓኅብረት አባል ሀገራት ውጭ ከሆኑ አገርት ተጨማሪ ተፈላጊ ባለሞያዎች ወደሀገሪቱ እንዲመጡ ማበረታታት ነው። 

 

ኂሩት መለሰ