1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን መብታቸው የተነፈገው ሀገር አልባዎች

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 20 2016

በብሪታንያ ባየርን የመሳሰሉ ባለሞያዎች የሀገር አልባዎቹን ታሪክ ያጠናሉ።በመጨረሻው የፍርድ ቤት ውሳኔ ላይም የባለሞያዎቹ ሃሳብ ይካተታል።በጀርመን ግን ውሳኔው የዳኞች ብቻ ነው። በጀርመን በአገር አልባነት ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሕጋዊ ደረጃ ያላቸው ሂደቶች የሉም።ስልጣኑ የማዘጋጃ ቤቶች ባለስልጣናት ነው።በተለያዩ ግዛቶች የተለያዩ ውሳኔዎች ይሰጣሉ።

https://p.dw.com/p/4YGEo
Christiana Bukalo - Mitgründerin der Menschenrechtsorganisation Staatefree
ምስል Dominik Morbitzer

በጀርመን መብታቸውን የተነፈጉት ሀገር አልባዎች

የጀርመን መንግሥት በጀርመን ዜግነት የሚሰጥበትን መንገድ ያቃልላል ያለውን አዲስ የዜግነት ሕግ ለማውጣት እየተዘጋጀ ነው። ይሁንና በሀገሪቱ ከሚገኙ ወደ 126 ሺህ ከሚጠጉ ሀገር አልባ ሰዎች አብዛኛዎቹ ይህ ምንም ለውጥ አይመጣም ይላሉ እንደ ዶቼቬለ ኦሊቨር ፒፐር ዘገባ ክርስቲና ቡካሎ ጀርመን ነው የተወለደችው ፤ ሆኖም የተመዘገበችው ሀገር አልባ ተብላ ነው። እንደ 29 ዓመቷ ክርስቲና ቡካሎ ጀርመን ተወልደው ሀገር አልባ በመሆናቸው በጀርመን የእለት ተዕለት ሕይወታቸው ፈተና የሆነባቸው ጥቂት አይደሉም። የባንክ ሂሳብ ለመክፈት ፣ ሆቴል ለመያዝ፣ ትዳር ለመመስረት ፣ እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኛ ለመሆን  መታወቂያ ያስፈልጋል። ይሁንና የትኛው ሀገር ነው ለዜግነት ለሌለው ሰው ፓስፖርት የሚሰጠው ?ትላለች ቡካሎ
«  ምክንያቱም በነጻነት ከአንዱ ወደሌላው አገር ለመጓዝ የጉዞ ሰነድ ያስፈልጋል። ስራ ለማግኘትም እንዲሁ ችግሮች ያጋጥማሉ። ከፍተኛ ትምሕርት መጀመርም እንዲሁ አዳጋች ነው። ያም ብቻ አይደለም መጨረሱም እንዲሁ። ከፍተኛ ትምሕርታቸውን እስከመጨረሻው ማጠናቀቅ ያልቻሉ ሰዎች አውቃለሁ። ምክንያቱም ለመጨረሻው ፈተና የልደት ማስረጃ ይጠየቃሉ። አገር አልባ ሰዎች በአንድ አገር ውስጥ እድሜያቸውን በሙሉ ቢኖሩም የመምረጥ መብት ግን የላቸውም።»


ቡካሎ የጀርመን ባለሥልጣናት ዜግነታቸውን ማረጋገጥ ካልቻሉት ከምዕራብ አፍሪቃ ከመጡ ወላጆች ነው የተወለደችው ። ጀርመን ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው ወደ 126 ሺህ ከሚጠጋ ሀገር አልባ ሰዎች አንዷ ናት። ሀገር አልባ ተብለው ጀርመን የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ከመካከላቸው በአሁኑ ጊዜ በዓለም ካርታ ላይ ሀገራቸው ያልተካተተ ፍልስጤማውያን ኩርዶች ወይም የቀድሞ የሶቭየት ኅብረት ወይም የዩጎዝላቭያ ግዛቶች ዜጎች ይገኙበታል። በአሁኑ ጊዜ «መንግሥት አልባ» የሚባል ድርጅት ተባባሪ መሥራች ክርስቲና ቡካሎ በማኅበሩ አማካይነት ሀገር አልባ ሰዎችን ትረዳለች። ቡካሎ እንደምትለው ሀገር አልባነት ምን ማለት እንደሆነ ያወቀችው ገና በለጋ እድሜዋ ነው። 
«ልጅም ሆነህ የማይገባህ ቦታ ነው የሚያስቀምጡህ። እዚህ መቆየት አትችልም፤በተመሳሳይ ሁኔታ ሀገሩንም ለቀህ መውጣት አትችልም። ትርጉም የሌላቸው ነገሮች ናቸው። ወደ ውጭ የሚደረጉ የተማሪዎች ልውውጥ፤ የቋንቋ ትምሕርትና ፣የበረዶ መንሸራተት ጉዞዎች በሙሉ ሊሆኑ አይችሉም።  እርግጥ ነው ይህን ሲሆን እጅግ ጠለቅ ካለ የውርደት ስሜትጋር ይገናኛል። ምክንያቱም ላንተ በግልጽ ያልተነገረህን ነገር ነው ማስረዳት ያለብህ።» የጀርመን የዜግነት ሕግ ማሻሻያና ተግዳሮቱ

 የጀርመኑ የኤስፔዴ ፓርቲ ፖለቲከኛ ስቫሳን ቼቢ አገር አልባ መደረግ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ነው ብለዋል። እርሳቸው አገር አልባ ከሆኑ ፍልስጤማዊ ወላጆቻቸው በርሊን ነው የተወለዱት 15 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ዜግነት አላገኙም ነበር።ባየር አገር አልባ ሰዎች ሰብዓዊ መብቶቻቸውን ተነፍገዋል በመባሉ ይስማማሉ።
በጀርመን እንደቡካሎ ሁሉ 30 ሺህ ሰዎች ሀገር አልባ ተብለው እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ያ ማለት ጀርመን ስድስት ዓመት ከኖሩ  ዜግነት እንዲሰጣቸው ማመልከት ይችላሉ።ግን ሌሎች አንድ መቶ ሺህ ግለ ሰቦች ዜግነታቸው ግልጽ አይደለም ተብለዋል፤ ከባንግላዴሽ እንደተባረሩት እንደ ሮሂንግያ ማንነታቸውን ማረጋገጥ የሚቻልበት ሰነድ የሌላለቸው ስደተኖች።ምስል statefree.world


ከሁለት ዓመት በፊት ቡካሎ ሀገር አልባ ለሆኑ ሰዎች ድምጽ ለመሆን «መንግሥት አልባ» የተባለውን የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሙኒክ ውስጥ መሠረተች ። ድርጅቱ የተቋቋመበት ዓላማም የችግሩ ሰለባ ለሆነው ሰፊ የኅብረተሰብ ክፍል መረጃ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለፖለቲከኞች ጥሪ ለማቅረብም ጭምር ነው። « ጀርመን ውስጥ የተወለዱ ሀገር አልባ ህጻናት ወዲያውኑ ሀገር አልባ ተብለው ነው የሚለዩት። በተመሳሳይ ሁኔታ የጀርመን ዜግነት የማግኘት መብት አላቸው። ይህ የሚሆነው በመጀመሪያዎቹ 5 ዓመታት ነው።» ጀርመን ውስጥ ዜግነት ለማግኘት የትውልድ ቦታ ሳይሆን የወላጆች ዜግነት ነው አስፈላጊው። ወላጆች ሀገር አልባ ከሆኑ ልጆችም ሀገር አልባ ናቸው። በዚህ የተነሳም ጀርመን ከሚገኙ ሀገር አልባዎች ከአንድ ሶስተኛ በላይ ህጻናት ናቸው። ቡካሎ ጀርመን የተወለዱ 65 ዓመት ሆኗቸውም አሁንም ሀገር አልባ የሆኑ ሰዎች ታውቃለች። የቡካሎ ድርጅት የመሀል ግራው የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ፣ የአረንጓዴዎቹና የነጻ ዴሞክራቶች ፓርቲ ተጣምረው የሚመሩት የጀርመን መንግሥት አዲስ የዜግነe አሰጣጥ ሕግ እንዲወጣ ባቀረበው ሀሳብ ትልቅ ተስፋ አለው።ይሁንና እስካሁን በማንኛውም ረቂቅ ሕግ ላይ የሀገር አልባ ሰዎች ጉዳይ አልታየም። ዶቼቬለ ስለነዚህ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጠየቃቸው የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ግን «የሀገር አልባ ሰዎች ስጋት በዜግነት ሕጉ በበቂ ሁኔታ ግምት ውስጥ ገብቷል፤ ከዚህ በተጨማሪም በዜግነት አሰጣጥ ሕጉ አገር አልባ ሰዎችም የውጭ ዜጋ ስለሆኑ በጀርመን ዜግነት ለማግኘት የተቀመጠው አጠቃላይ ደንቦች ለሀገር አልባሰዎችም ይሰራል» ብለዋል።
ፈጣን የዜግነት አሰጣጥና በከፍተኛ ደረጃ ለሰለጠኑ የውጭ ዜጎች ማበረታታዎችን ያካተተው የአዲሱ የዜግነት ሕግ ማሻሻያ የቀረበው የፍልሰትና ፍልሰተኞች ጉዳይ በጀርመን የፖለቲካ አጀንዳ ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ በያዘበት ወቅትነው። ቡካሎ የጀመረችው ዘመቻ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉ አላስገረማትም። አዲሱ የጀርመን ረቂቅ የፍልሰት ሕግ«ይህን የምገልጸው፣ በአንድ በኩል በፖለቲካው ፣ስለ አገር አልባ ሰዎች የእውቀት ማነስ መኖሩን ነው።በሌላ በኩል ደግሞ በአውሮጳ አጠቃላዩ የፖለቲካ ሁኔታ ወደ ቀኝ እንዳዘነበለ ነው። በአሁኑ ጊዜ ተራማጅ የሚባሉ የጀርመን ፓርቲዎች ከነዚህ ፣ በስፔይን ወይም በፖርቱጋል ለረዥም ጊዜ ባሉበት ለዘለቁት ለእነዚህ ተራማጅ ጉዳዮች ድጋፍ ለመስጠት ተቸግረዋል። »በእስያዊቷ ሀገር ባንግላዴሽ በአንድ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ወደ 700 ሺህ የሚጠጉ ሀገር አልባ የሮሂንግያ ስደተኞች ይገኛሉ። ጁዲት ባየር ደቡብ ጀርመን በሚገኘው በኮንስታንዝ ዩኒቨርስቲ የስነ-ሰብ ጥናት መምህር የዛሬ 7 ዓመት 700 ሺህ የሮሂንግያ አናሳ ሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት ሕይወታቸውን ለማዳን ከሸሹበት ከዛሬ ሰባት ዓመት አንስቶ የሀገር አልባ ሰዎችን ጉዳይ ይከታተላሉ። የሮሂንግያ አናሳ ሙስሊሞች አሁን በዓለም አቀፍ ሕግ ሀገር አልባ በሚባሉባት በባንግላዴሽ ነው የሚኖሩት። ባየር በአንድ የብሪታንያ ፍርድቤት በሚካሄድ የአገር አልባ ሰዎች ጉዳይ በሚታይበት ሂደት ላይ በሙያቸው በምስክርነት ይሰራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት በጀርመን ኅብረተሰቡ ስለ ጉዳዩ ያለው ግንዛቤ አናሳ ነው።
« በጀርመን አገር አልባነት ህዝቡ እይታ ውስጥ ያልገባ ችግር ነው።በመጨረሻም በሌላኛው ጫፍ በሚቀመጠው ሰው ነው የሚወሰነው። ይህ ብዙ አገር-አልባ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚማረሩበት ጉዳይ ነው። ምንም ዓይነት ሕጋዊ ዋስትና የለም፤ በግለሰቦች እና በዕውቀት ደረጃቸው ላይ የተመረኮዘ ነው። ብዙውን ጊዜ በፍጹምመጥፎ ዓላማ ኖሯቸው አይደለም፤ ይልቁንም በቀላሉ የአገር አልባዎችን ጉዳይ እንዴት መመልከት እንዳለባቸው የእውቀት ደረጃቸው ያነሰ በመሆኑ እንጂ።» ፍርድ ቤቶችን ብንወስድ ለምሳሌ በብሪታንያ ባየርን የመሳሰሉ ባለሞያዎች የሀገር አልባዎቹን ታሪክ ያጠናሉ። በመጨረሻው ውሳኔ ላይ የባለሞያዎቹ ሃሳብም ይካተታል።በጀርመን ግን ውሳኔው የዳኞች ብቻ ነው። በጀርመን በአገር አልባነት ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሕጋዊ ደረጃ ያላቸው ሂደቶች የሉም። ስልጣኑ የማዘጋጃ ቤቶች ባለስልጣናት ነው። ይህም ማለት አንዳንዴ ሙኒክ የሚገኝ ህዝብ ከሀምቡርግ ወይም ከኮሎኝ የተለየ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል።

የሮሂንግያ አናሳ ሙስሊሞች አሁን በዓለም አቀፍ ሕግ ሀገር አልባ በሚባሉባት በባንግላዴሽ ነው የሚኖሩት። ባየር በአንድ የብሪታንያ ፍርድቤት በሚካሄድ የአገር አልባ ሰዎች ጉዳይ በሚታይበት ሂደት ላይ በሙያቸው በምስክርነት ይሰራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት በጀርመን ኅብረተሰቡ ስለ ጉዳዩ ያለው ግንዛቤ አናሳ ነው።
ጁዲት ባየር ደቡብ ጀርመን በሚገኘው በኮንስታንዝ ዩኒቨርስቲ የስነ-ሰብ ጥናት መምህር የዛሬ 7 ዓመት 700 ሺህ የሮሂንግያ አናሳ ሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት ሕይወታቸውን ለማዳን ከሸሹበት ከዛሬ ሰባት ዓመት አንስቶ የሀገር አልባ ሰዎችን ጉዳይ ይከታተላሉ። ምስል DW
የባንክ ሂሳብ ለመክፈት ፣ ሆቴል ለመያዝ፣ ትዳር ለመመስረት ፣ እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኛ ለመሆን  መታወቂያ ያስፈልጋል። ይሁንና የትኛው ሀገር ነው ለዜግነት ለሌለው ሰው ፓስፖርት የሚሰጠው ?ትላለች ቡካሎ
 ክርስቲና ቡካሎ ጀርመን ነው የተወለደችው ፤ ሆኖም የተመዘገበችው ሀገር አልባ ተብላ ነው። እንደ 29 ዓመቷ ክርስቲና ቡካሎ ጀርመን ተወልደው ሀገር አልባ በመሆናቸው በጀርመን የእለት ተዕለት ሕይወታቸው ፈተና የሆነባቸው ጥቂት አይደሉም። ምስል Nemanja Rujevic/DW

« መሠረታዊው ነገር ጉዳዩ ውሳኔ በሚሰጠው ሰው ላይ የተመመረኮዘ ነው።

በጀርመን እንደቡካሎ ሁሉ 30 ሺህ ሰዎች ሀገር አልባ ተብለው እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ያ ማለት ጀርመን ስድስት ዓመት ከኖሩ  ዜግነት እንዲሰጣቸው ማመልከት ይችላሉ።ግን ሌሎች አንድ መቶ ሺህ ግለ ሰቦች ዜግነታቸው ግልጽ አይደለም ተብለዋል፤ ከባንግላዴሽ እንደተባረሩት እንደ ሮሂንግያ ማንነታቸውን ማረጋገጥ የሚቻልበት ሰነድ የሌላለቸው ስደተኖች።

አንድ የጀርመኑ የኤስፔዴ ፓርቲ ፖለቲከኛ ስቫሳን ቼቢ አገር አልባ መደረግ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ነው ብለዋል። እርሳቸው በርሊን የተወለዱ አገር አልባ ከሆኑ ፍልስጤማዊ ወላጆቻቸውነው የተወለዱት 15 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ዜግነት አላገኙም ነበር።ባየር አገር አልባ ሰዎች ሰብዓዊ መብቶቻቸውን ተነፍገዋል በመባሉ ይስማማሉ።በጀርመን የውጭ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃትና መከላከያው

«ሰብዓዊ መብቶች ሊከበሩ የሚችሉት በፖለቲካ መዋቅር ይህም ማለት በመንግስት ፖለቲካዊ ፈቃደንነት ብቻ ነው።  ይህም ማለትፈላስፋዋ ሀና አረንድት እንዳስቀመጡት  ሀገር አልባ ሰዎች ብዙውን ጊዜ መብቶችን የማግኘት መብት ይነፈጋሉ።

« መሠረታዊው ነገር ጉዳዩ ውሳኔ በሚሰጠው ሰው ላይ የተመመረኮዘ ነው።

በጀርመን እንደቡካሎ ሁሉ 30 ሺህ ሰዎች ሀገር አልባ ተብለው እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ያ ማለት ጀርመን ስድስት ዓመት ከኖሩ  ዜግነት እንዲሰጣቸው ማመልከት ይችላሉ።ግን ሌሎች አንድ መቶ ሺህ ግለ ሰቦች ዜግነታቸው ግልጽ አይደለም ተብለዋል፤ ከባንግላዴሽ እንደተባረሩት እንደ ሮሂንግያ ማንነታቸውን ማረጋገጥ የሚቻልበት ሰነድ የሌላለቸው ስደተኖች።

አንድ የጀርመኑ የኤስፔዴ ፓርቲ ፖለቲከኛ ስቫሳን ቼቢ አገር አልባ መደረግ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ነው ብለዋል። እርሳቸው በርሊን የተወለዱ አገር አልባ ከሆኑ ፍልስጤማዊ ወላጆቻቸውነው የተወለዱት 15 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ዜግነት አላገኙም ነበር።ባየር አገር አልባ ሰዎች ሰብዓዊ መብቶቻቸውን ተነፍገዋል በመባሉ ይስማማሉ።

«ሰብዓዊ መብቶች ሊከበሩ የሚችሉት በፖለቲካ መዋቅር ይህም ማለት በመንግስት ፖለቲካዊ ፈቃደንነት ብቻ ነው።  ይህም ማለትፈላስፋዋ ሀና አረንድት እንዳስቀመጡት  ሀገር አልባ ሰዎች ብዙውን ጊዜ መብቶችን የማግኘት መብት ይነፈጋሉ።

 

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ