1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዩክሬን ጦርነት የጀርመን ሚና

ማክሰኞ፣ የካቲት 14 2015

መጀመሪያ ላይ ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ ከደገፉት ጀርመናውያን መካከል በመራዘሙና ባስከተላቸው ልዩ ልዩ ችግሮች ምክንያት ተሰላችተው አሁን ጦርነቱ እንዲቆም የሚጠይቁ ጥቂት አይደሉም። ለዚህም እንደ ምክንያት ከሚነሱት ውስጥ ወደ ጀርመን የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር እጅግ እየጨመረ መሄድ እንዲሁም እለት ተእለት እየተባባሰ የሄደው የኑሮ ውድነት ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/4NntQ
Deutschland Ukraine Bundeskanzler Olaf Scholz und Präsident Wolodymyr Selenskyj
ምስል SERGEI SUPINSKY/AFP/Getty Images

በዩክሬን ጦርነት የጀርመን ሚና

የዩክሬኑ ጦርነት የፊታችንን አርብ አንድ ዓመት ይደፍናል ።ዓመት ይዘልቃል ተብሎ ያልተገመተው ጦርነቱ የአስር ሺህዎችን ሕይወት አጥፍቶ ሚሊዮኖችን አሰገድዶ በርካታ ንብረትም አውድሞ አሁንም ቀጥሏል።ጦርነቱ በዩክሬን አሸናፊነት እንዲጠቃለል የሚሻው ምዕራቡ ዓለም ለዩክሬን ከፍተኛ ወታደራዊ ድጋፍ እያደረገ ነው። ዩክሬንን በምትወጋው በሩስያ ላይም ልዩ ልዩ ማዕቀቦችን ጥሏል። ሩስያ ለምትወጋት ለዩክሬን ብዙ ወታደራዊ ድጋፍ ከሚሰጡ የአውሮጳ ሀገራት አንዷ ጀርመን ናት።ጀርመን ለዩክሬን ከላከችው ድጋፍ ውስጥ ከተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችና ከወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እንስቶ እስከ ሮኬት ማስወንጨፊያዎች እና የአየር መከላከያ ስርዓቶች ድረስ ይገኙበታል። የጦርነቱን አካሄድ ይቀይራል ተብሎ በሰፊው የተነገረለት ሊዮፓርድ 2 A 6 የተባለውን የውጊያ ታንክም ለዩክሬን ለመላክም ቃል ገብታለች ።በዩክሬን ጦርነት የጀርመን ሚና ምን እደሆነ ዶቼቬለ የጠየቃቸው ጀርመን የሚኖሩና የሚሰሩት ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ የሕግ ባለሞያና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እንዳሉት የብዙዎች ፍላጎት ጀርመን በዩክሬኑ ጦርነት የመሪነቱን ቦታ እንድትይዝ ነበር። ሆኖም ጦርነቱ ውስጥ ብቻዋን የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ያሳወቀችው ጀርመን ከዚያ ይልቅ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በመሆን ዩክሬንን መደገፍን መርጣለች።በዚህ መሠረትም በርካታ ወታደራዊ ድጋፎችን እንደሰጠችና ድጋፏንም አጠናክራ መቀጠሏን ዶክ,ር ለማ ያስረዳሉ።መጀመሪያ ላይ ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ ከደገፉት ጀርመናውያን መካከል በመራዘሙና ባስከተላቸው ልዩ ልዩ ችግሮች ምክንያት ተሰላችተው ጦርነቱ እንዲቆም የሚጠይቁ ጥቂት አይደሉም። ለዚህም እንደ ምክንያት ከሚነሱት ውስጥ ወደ ጀርመን የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር እጅግ እየጨመረ መሄድ እንዲሁም እለት ተእለት እየተባባሰ የሄደው የኑሮ ውድነት ይገኙበታል። ዶክተር ለማ ጦርነቱን የሚቃወሙ ፓርቲዎችም ግፊታቸውን እያጠናከሩ በመሄድ ላይ ናመሆናቸውን ነው የገለጹት።

Deutschland Waffen für die Ukraine
ጀርመን ሰራሾቹ ሊዮፓርድ 2 ታንኮችምስል Martin Meissner/AP Photo/picture alliance

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ