ሐማስ እስራኤላውያንን ከገደለ በኋላ ጀርመን የሰጠችው ምላሽ ዲፕሎማሲያዊ ግፊትን ማስነሳት ነበር ። ጥቃቱ ከተፈጸመ ከጥቂት ቀናት በኋላ መራሔ መንግስት ኦላፍ ሾልስ ለጀርመን ፓርላማ ለሰላም ጠንክረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ከጋዛ ጋር ግኑኝነት ካላቸው ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ጋር የቅርብ ግንኙነት አለኝ ። ዛሬ ደግሞ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋንን እናግራለሁ ። ከዚህም በተጨማሪ ሀገራቱን በማሸማገል ቁልፍ ሚና የምትጫወተውን የኳታር ዓሚርን ተቀብዬ አነጋግራለሁ።
ከዚያ ብዙም ሳይቆዩ ሾልስ እራሳቸው ወደ እስራኤል ተጉዘዋል ።
ሾልስ ለቤንጃሚን ኔታንያሁ በጥቃቱ የተሰማቸውን ሐዘን ቢገልጹም ግጭቱ እንዲስፋፋ እንደማይፈልጉም ተናግረዋል።
" ጠቅላይ ሚኒስትር! መንግሥቴ ይህ ግጭት እንዳይባባስ ሁሉንም ነገር እያደረገ ነው ። በቀጠናው እሳት እንዳይቀጣጠል መከላከል አስፈላጊ ነው "
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሊናና ቤርቦክም ምስቅልቅሉን ለመፍታት ወደ ዮርዳኖስን ፣ እስራኤል ፣ ሊባኖስ እና ግብፅን በመጓዝ የተጠናከረ ዲፕሎማሲ አካሂደዋል ።
ከጀርመን የውጭ ፖሊሲ ምክርቤት ማሪያ ሚዩለር ስለጉዳዩ ተታዮን ብለዋል
"በእርግጥ ከሌሎች የአውሮፓ መሪዎች ሁሉ አስፈላጊ ሚና ተጫውተናል። ይሁንና ጉዳዩን በዚህ ይዘት ብናየውስ በኔ እይታ ዋናዋ ባለድርሻ አሜሪካ ናት።``
በመካከለኛው ምሥራቅ በሚመለከት፤ ጀርመን ገለልተኛ አገር አይደለችም ። የአይሁዳውያን የናዚ እልቂት ጀርመናውያን የሚል ትርጉም አለው። ይህም ከእስራኤላውያን ጋር የመቆም ልዩ ኃላፊነት ይጥልባታል ፤ በተለይ ደግሞ ዛቻ በሚሰነዘርበት ጊዜ እንዲህ ከማድረግ ወደኋላ አትልም ።
ይህም የሆነው አንጌላ ሜርክል እ.ኤ.አ በ2008 ለእስራኤሉ ምክርቤት ባደረጉት ንግግር ነው ። እሳቸው እንዳሉት እስራኤልን መታደግ የጀርመን ብሔራዊ ጥቅም አካል ነው። እስከአሁንም የጀርመን የፖሊሲ መርህ ነው።
ከጀርመን የውጭ ፖሊሲ ምክርቤት ማሪያ ሚዩለር እንደሚሉት
``በአሁኑ ሰአት ጀርመን ለእስራኤል ደህንነት ካላት ቁርጠኝነት አንጻር አሸማጋይ የመሁን ችግር ይኖረዋል። አለአይደል ከእስራኤል ወገን ነን ። እርግጥ ነው በዚህ ወሳኝ ወቅት እስራኤልን ልንቀፋቸው እንደማንችል ከተናገሩ አገሮች መካከል ጀርመን አንዷ ነበረች ። "
በተመሳሳይ የጀርመን መሪዎች በፍልስጤም መሪ መሐመድ አባስ ጊዜ ከፍልስጤም ጋር የረዥም ጊዜ የጠበቀ ግንኙነት አላቸው። ጀርመን በአውሮፓ ተጽዕኖ ፈጣሪና ለጋሽ አገር ተደርጋ ትወሰዳለች፤ ከእየሩሳሌም መሪዎች ጋር ያላት የጠበቀ ወዳጅነትም እንዲሁ።
በርሊን ከዓረብ እና ከሙስሊም አገራት ጋር የጠበቀ ወዳጅነት አላት፤ ይህ ሰላምን ለማፈላለግ ይጠቅም ይሁን? ማሪያ ሚዩለር
"ከሱኒ አረብ ሃገራት ፣ እንደ ግብፅ ፣ ዮርዳኖስ ጥሩ ግኑኝነት አለን። ከኳታርና ከቱርክ ጋር እየተነጋገርን ነው ፤ እነሱም ኢራንም ጋር ግንኙነት አላቸው ፤ ስለዚህ ከኢራን ጋር ይነጋገራሉ ።"
የጀርመን መንግሥት በአሁኑ ጊዜ ባለው ግጭት ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ቢያንስ ስምንት የጀርመን ዜጎች ከሐማስ እገታ የሚወጡት ዕጣ ፈንታ ላይ ነው ።
በተጨማሪም በጋዛ የሚኖሩ ከመቶ በላይ ጀርመናውያንን ለመጠበቅ እየተሰራ ነው ።
ጀርመን እነዚህን ዜጎች ከአደጋ ለማዳንና ደም አፋሳሹን ግጭት ለማስቆም ሁሉንም ዘዴዎች እየተጠቀመች ነው ።