1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

በአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዚዳታዊ ዕጩዎች ክርክር

ዓርብ፣ ኅዳር 28 2016

በአሜሪካ ቀጣዩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲውን ለመወከል የቀረቡ ዕጩዎች የመጨረሻውን ክርክር ሰሞኑን በአላባማ አካሂደዋል።በመጭው የሀገሪቱ ምርጫ ይወዳደራሉ ተብለው የሚጠበቁት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ግን በአላባማው ክርክር አልተሳተፉም ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4ZwBX
ዩናይት ስቴትስ ነጬ ቤተ መንግሥት
ዩናይት ስቴትስ ነጬ ቤተ መንግሥት ምስል Samuel Corum/Getty Images

የአሜሪካ የምርጫ ክርክር በአለባማ ግዛት

በዩናይትድ ስቴትስ ከዋናው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አስቀድሞ፣ በየክፍለግዛቶቹና የአካባቢ አስተዳደሮች የሚካሄደው የዕጩዎች የምረጡኝ ዘመቻ ተጧጡፎ እየተካሄደ ነው።
በሃገሪቱ የምርጫ ስርዓት፣የፓርቲ ዕጩ ሆኖ ለመቅረብ የየክፍለግዛቶችና የአካባቢ አስተዳደር ተወካዮችን ድምጽ ማግኘት አንደኛው ቅድመ ሁኔታ ነው።ሰሞኑን  ለመጨረሻ ጊዜ የአላባ ዩኒቨርሲቲ ያስተናገደው፣አራተኛው የዕጩዎች ክርክር ለሁለት ሰዐታት ያህል የዘለቀና በዕጩዎቹ መኻከል ከባድ ፍጥጫ የታየበት ነበር።

አራቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩዎች

በዙሁ መድረክ ላይ፣በተባበሩት መንግስታት የቀድሞ የዩናይትድስቴትስ አምባሳደር ኒኪ ሄሊ፣የቀድሞ የኒውጀርሲ ሃገረ ግዛት ገዢ ክሪስ ክሪስቲ፣የፍሎሪዳው አስተዳዳሪ ሮን ዴሳንተስ እና ስራ ፈጣሪው ባለሃብት ቪቬክ ራማስዋሚ ተሳትፈዋል። በቀደሙት ክርክሮች ሁሉም እጩዎቹ ቀዳሚ ኢላማ የነበራቸው ሲሆን፤ትናንት ምሽት ደግሞ ወይዘሮ ሔሊ ላይ በማተኮር ሞግተዋቸዋል።የቀድሞዋ የደቡብ ካሮላይና ገዥ እና የተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር ኒኪ ሔሊ፣ ከሚስተር ትራምፕ በጣም ርቀው በሁለተኛ ደረጃ ላይ ቢገኙም በቅርብ ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት ደረጃቸውን አሻሽለው ታይተዋል። እርሳቸውም፣የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ስኬታቸውን በማስረዳት ከሁሉም የተሻሉ መሆናቸውን ይናገራሉ።
"በህይወት ዘመኔ ሁሉ ወግ አጥባቂ ታጋይ ነኝ።" አምባሳደር ሔሊ በትራምፕ የስልጣን ዘመን የነበራቸውን፣በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር
ኃላፊነት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ይታወቃል። በዶናልድ ትራምፕ ላይ የሰላ ትችት በማቅረብ የሚታወቁት ሚስተር ክሪስቲ በበኩላቸው፣ ትናንት ምሽት ተቀናቃኞቻቸው እንደእርሳቸው ሁሉ ሚስተር ትራምፕን እንዲያወግዙ ሲገፋፉዋቸው ነበር፣ይሁንና ብዙም አልተሳካላቸውም። ክሪስቲ ሐቅ ይዤ ወደምርጫው የመጣሁት እኔ ነኝ ይላሉ።
"ብዙውን ጊዜ በዚህ መድረክ ላይ እውነትን የሚናገር ብቸኛው ሰው መሆን በጣም ከባድ ነው።"ሚስተር ሮን ዴሳንቲስ በፍሎሪዳ አስተዳዳሪነታቸው አመጣሁት ላሉት ስኬት አፅንዖት ሰጥተዋል።ወጣቱ ባለሃብት ሚስተር ራማስዋሚ በአቀራረባቸው አወዛጋቢ ሆነው አምሽተዋል።" በነጩ ቤተመንግስት ውስጥ፣ፍጹም ቆራጥ የሆነ ሰው እንፈልጋለን።"
ራማስዋሚ፣ወይዘሮ ሄሊን በሙስና ፤ ሚስተር ክሪስቲን ደግሞ ፋሺስት ናቸው ሲሉ ከሰዋቸል።ሚስተር ክሪስቲ በምላሹ፣ሚስተር ራማስዋሚን “ለትንሽ ጊዜ ዝም ይበሉ” በማለት ምላሽ
ሰጥተዋቸዋል። 

ዶናልድ ትራምፕ
ዶናልድ ትራምፕምስል Butch Dill/AP/picture alliance

አምባሳደር ሄሊ ደግሞ የተለየ አቀራረብ በመያዝ፣ለሚስተር ራማስዋሚ ምላሽ የመስጠት እድል ሲሰጣቸው፣ “ለእርሱ ምላሽ ለመስጠት ጊዜዬን
አላባክንም ” ብለዋል።በትናንቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩዎች ክርክር ላይ፣የሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ግሽበትና የጤና አጠባበቅፖሊሲ አማራጮች ተነስተዋል።በእስራኤልና በዩክሬን ስለሚካሄዱት ጦርነቶችም ዕጩዎቹ ዐሳቦቻቸውን አሰምተዋል።በአሜሪካ ዕለት ከዕለት ስለተስፋፋውና የዜጎች ስጋት ስለሆነው፣ የጅምላ ግድያ የጦር መሣሪያ ወንጀልግን ያሉት ነገር የለም።ከመጨረሻው ክርክር በኃላ፣በቀጣዩ ጥር ወር አጋማሽ ላይ "ካውካስ" ተብሎ የሚታወቀው በፖለቲካ
ፓርቲዎች የሚካሄደው የዕጩዎች ምርጫ የሚጠበቅ ነው።

የትራምፕ መሪነት

የቀድሞው ፕሬዚደንት ከዚህ ቀደም በተደረጉት ሶስት ክርክሮች ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ባለመሆናቸውየሪፐብሊካን ፓርቲ ዝግጅቱን እንዲሰርዝ ከመጠየቃቸው በላይ አላባማ ላይ በተዘጋጀውመድረክ አልተገኙም።በብሔራዊውም ሆነ በየግዛቶቹ አስቀድሞ በተካሄደው ምርጫዎች፣ተቀኛቃኞቻቸውን በሁለት ዕጥፍ
እየመሩ መሆኑ የተነገረላቸው ዶናልድ ትራምፕ፣ ሌላ እጩ ባለሁለት አሃዝ መሪነታቸውን ማሸነፍእንደማይችል አመልክተዋል።በዚህ የተነሳ በዋናው ፕሪዚዳንታዊ ምርጫ፣ትራምፕ ከኘራዚዳንት ጆሴፍ ባይደን ጋር እንደገና ለውድድር እንደሚቀርቡ ብዙዎች ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

 

ታሪኩ ኃይሉ 

ፀሀይ ጫኔ 

አዜብ ታደሰ