1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአሜሪካ ማሪዋናን እንደመድኃኒት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 21 2009

በዩናይትድ ስቴትስ 28 ክፍለ ግዛቶች ማሪዋናን ለህክምና መጠቀም የተፈቀደ ሲሆን ዋሽንግተንን ጨምሮ ስምንት ግዛቶች አጽድቀዉ እየተጠቀሙበት መሆኑን ከስፍራዉ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል። የህክምናና ጥንታዊ ስሙ ካናቢስ የሚባለዉ ማሪዋና በኢትዮጵያ እና መካከለኛዉ ምሥራቅ አካባቢ ሃሽሽ በመባል ይታወቃል

https://p.dw.com/p/2V0U8
USA Marihuana
ምስል picture alliance/newscom/D. Benton

MMT-Ber.D.C. (Medical Marijuana in USA+) - MP3-Stereo

። በብዙ ሃገራት በአደንዛዥ ዕፅነት የተፈረጀ ሲሆን ኦፒየም ሄሮይን እና ኮኬይን ከሚባሉት አደገኛ ዕፆች ተርታ የተመደበ ነበር። አሜሪካን ዉስጥ ይህን ዕፅ እንደመድኃኒት የሚጠቀሙ ቁጥራቸዉ ቀላል እንዳልሆነ መክብብ ሸዋ በላከልን ዘገባ ጠቅሷል። መድኃኒት ላልተገኘላቸዉ መፍትሄ አልባ በሽታዎች እና መድኃኒትን ለማይቀበሉ የሰዉነት አካላት እንደመጨረሻ መፍትሄ የሚወሰድ መሆኑንም ተነግሯል። መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ