1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«በሴቶች ላይ የሚደርሱ ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ ጥቃቶች አሳሳቢ ናቸው።»

ዓርብ፣ ጥቅምት 29 2017

በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ በቪዲዮ እየቀረፁ መድፈርን ጨምሮ ከሀይማኖት ፣ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ ከአሰቃቂ ጥቃቶች መፈፀማቸው ተደጋግሞ ይሰማል። ያም ሆኖ በመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የአንድ ሰሞን አጀንዳ ከማድረግ ባለፈ ችግሩን በተመለከተ መሰረታዊ እና ተከታታይነት ያለው ስራ እየተሰራ አይደለም በሚል ይተቻሉ።

https://p.dw.com/p/4moNb
Hände
ምስል Colourbox

«በሴቶች ላይ የሚደርሱ ከባህልም ከሞራልም ውጭ የሆኑ ጥቃቶች አሳሳቢ ናቸው።»

በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ  የሚደርሰው ጥቃት በአይነትም በመጠንም እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል።በቪዲዮ እየቀረፁ መድፈርን ጨምሮ  በሴቶች ላይ ከሀይማኖት ፣ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ ከአሰቃቂ ጥቃቶች መፈፀማቸው ተደጋግሞ ይሰማል።በኢትዮጵያ በተለይም ግጭት በሚካሄድባቸው አከባቢዎች ሴቶችና ህጻናት ለተለያዩ  ፆታዊ ጥቃቶች  ተጋላጭ  መሆናቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች ዘገባዎች ያሳያሉ። 

ያም ሆኖ በመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የአንድ ሰሞን አጀንዳ ከማድረግ ባለፈ ችግሩን በተመለከተ መሰረታዊ እና ተከታታይነት ያለው ስራ እየተሰራ አይደለም  በሚል ይተቻሉ።

በህግ ሂደቱ በኩልም፤ ወንጀለኞቹ ብዙ ጊዜ አይያዙም ከተያዙም  ተመጣጣኝ ቅጣት አይሰጥም በሚል የአፈፃጸም እና የህግ ክፍተት ተደጋግሞ ይነሳል። በዚህ ሳምንት የአንድ ለአንድ ዝግጅት በአሳሳቢው የሴቶች ጥቃት ላይ  በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሴቶች፣ የህፃናት ፣የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሃዋሪያት እንግዳ አድርጓል። 

 ኮሚሽነር ፤ ርግበ ገብረሐዋሪያ
ርግበ ገብረሐዋሪያ ፤በኢሰመኮ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ምስል Privat

በኢሰመኮ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ ጥቃቶች ኮሚሽኑን እንደሚያሳስበው ገልፀዋል።

 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው እንዲያደምጡ እንጋብዛለን።

ፀሀይ ጫኔ
ነጋሽ መሀመድ