1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሙዚቃ ስለኮሮና ማስተማር

ዓርብ፣ ግንቦት 13 2013

በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ኢዛት እና ሩሃማ የራፕ እና ሂፕ ሆፕ የሙዚቃ ስልትን እየተጠቀሙ እና በቅብብሎሽ እየዘፈኑ ተማሪዎች ራሳቸውን ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ እንዲጠብቁ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/3tXPO
Äthiopien Corona  Mit Rap Musik auf Covid-19 aufmerksam machen
ምስል S. Wegayehu/DW

በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ጓደኛሞቹ ኢዛት ወግደረስ እና ሩሃማ ከድር ሁለቱም 13 ዓመታቸው ነው። የ7ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት እነዚህ ታዳጊዎቹ የራፕ እና ሂፕ ሆፕ የሙዚቃ ስልትን እየተጠቀሙ እና በቅብብሎሽ እየዘፈኑ ተማሪዎች ራሳቸውን ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ እንዲጠብቁ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።  የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ሁለቱ ጓደኛሞች ወደ ሚማሩበት ትምህርት ቤት በመሄድ ተሰጥዋቸውን ተመልክታለች።  ወደ መድረክ በመውጣት የሚፈልጉትን መልዕክት በዘፈን ማስተላለፍ መቻላቸው በራስ የመተማመን ስሜት ፈጥሮላቸዋል። በተሰመሳሳይ የእድሜ ክልል የሚገኙ ልጆችም በውስጣቸው ያለውን ፍላጎት አውጥተው ማሳየት አለባቸው ይላሉ። 

ሊሻን ዳኜ