ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ
በሃማስ ጥቃት በርካታ ቤተ እስራኤላዉያን ተገድለዋል ተባለ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2016ማስታወቂያ
በዩናይትድ ስቴትስ፣ በአውሮጳ ኅብረት፣ በጀርመን እና በሌሎች ሃገራት «አሸባሪ ድርጅት» ተብሎ የተፈረጀዉ በፍልስጤሙ ሐማስ የተገደሉ እስራኤላዉያን ቁጥር ከ1,200 በላይ መድረሱ እየተዘገበ ነዉ። የእስራኤል ጦር ጋዛ ሰርጥን በቦምብና ሚሳዬል መደብደቡን ዛሬም ለ 6 ኛ ቀን እንደቀጠለ ነዉ። የተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ድርጅቶች ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃና ከለላ እንዲደረግ የሚጠይቀዉ ዓለም አቀፍ ሕግ እንዲከበር እያሳሰቡ ነዉ።
እስራኤል በአጸፌታው በጋዛ ሠርጥ በከፈተችው የመልሶ ማጥቃት የአየር ጥቃት ዘመቻ ህጻናትን ጨምሮ ከ1350 በላይ ፍልስጤማዉያን መገደላቸዉም በሌላ በኩል እስራኤል ሃማስ ላደረሰዉ ጥቃት ምላሽ በጋዛ ሰርጥ እያደረሰች ካለዉ የአየር ድብደባ በተጨማሪ ጋዛ ላይ የኤሌትሪክ የጋዝ እና የመጠጥ ዉኃ አቅርቦትም መቋረጡ ተዘግቧል።
የእስራኤልና የሐማስ ጦርነት፤ የመንግስታት ዉዝግብ
በአሸባሪነት የተፈረጀዉ የሃማስ ቡድን በእስራኤል ባደረሰዉ ከእስራኤላዉያንን ጨምሮ ከዩናይትድ ስቴትስ ፤ ከእንጊሊዝ ፤ ከፈረንሳይ የመጡ ዜጎች ተገድለዋል። ከመቶ በላይ ዜጎች በሃማስ ታፍነዉ ተወስደዋል። ከሟቾች መካከከል በርካታ ቤተ እስራኤላዉያንም ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ ቤተ እስራኤላዉያን ተናግረዋል።
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ