ኤኮኖሚአፍሪቃሶማሊያ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ከተሰረዘላት በኋላ 100 ሚሊዮን ዶላር ብድር ጸድቆላታልTo play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 videoኤኮኖሚአፍሪቃEshete Bekele10 ታኅሣሥ 2016ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 10 2016ባለፈው ሣምንት ከፍተኛ መጠን ያለው ዕዳ የተሰረዘላት ሶማሊያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት 100 ሚሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦት ጸድቆላታል። የሶማሊያ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ከተሰረዘ በኋላ ዜጎቿ ኤኮኖሚው ያንሰራራል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል። በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የጸደቀው የዕዳ ስረዛ የሶማሊያን የውጭ ብድር ከ5.3 ቢሊዮን ዶላር ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር ቀንሶታል። ውሳኔውን የሰሙ የሶማሊያ ዜጎች ባረጀው ምትክ የመገበያያ ገንዘብ እንዲታተም ይሻሉ። https://p.dw.com/p/4aOQiማስታወቂያ