1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 14 2016

22ኛ ሣምንቱን በያዘው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጨዋታ በሳምንቱ መጨረሻ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡናና መቻል 1 - 1 በመለያየት ነጥብ ተጋርተው ውጥተዋል። እንግሊዝ ፕሪምየርሊግ በሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታዎች ሊቨርፑል ኤቨርተን ክርስታል ፓላስ እናአስቶን ቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሽንፈዋል። ኤፍ ኤ ካፕ ማንችስተር ዪናትድና ማንችስተር ሲቲ ለዋንጫ ይፋለምሉ።

https://p.dw.com/p/4f3GK
የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን
የቤጂንግ ግማሽ ማራቶንምስል ChinaImages/Sipa USA/picture alliance

የሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የስፖርት መሰናዶ

የሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የስፖርት መሰናዶ 

አትሊቲክስ  

የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ  ተካሄደ፡፡ በውድድሩ ከ10 ሺህ በላይ ኀካፋዮች እንዲሁም ከ22 ክለቦች የተወጣጡ አትሌቶች ተሳትፈዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ያዘጋጁት ይህ ዉድድር መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጓል።  በወንዶች ምድብ አትሌት ገመቹ ዲዳ በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ÷ በሴቶች ደግሞ ጌጤ አለማየሁ አሸንፋለች።

የ 2024 ሎንዶን ማራቶን ትላንት ተካሄዶ ነበር በውጤቱም  ኬኛዊው የ 27 ዓመቱ አትሊት  አሌክሳንደር ሙንያዎ   2፣04፣01፣00 በመግባት ቀዳሚ  ሆንዋል አትሊትቀነኒሳ በቀለ  2፡04፡15፡00  ሁለተኛ ሲሆንእንግሊዛዊው አትሊትሌት ኢሚለ ቼረስ   2፡06፡46፡00 ሶስተኛ ሆንዋል።

አትሌትቀነኒሳ በቀለ በ41 ዓመቱ  በለንደን የተካሄደየማራቶን ውድድርን በ2ኛነት ለማጠናቀቅ ባሳየው ትጋት እና ብቃት የ በርካቶችን አድናቆት አትርፎዋል። አንጋፋውአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የለንደን ማራቶን ውድድርን 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ  ከ2019 ወዲህከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ የተመዘገበ የመጀመሪያው ሰአት በመሆን ተመዝግቦዋል።

በዚህ ውድድር ኤርትራዊው አትሊት ሄኖክ ተስፋይ 6ኛ ሁኗል  ሊላው ኢትዮጵያዊአትሊት ክንዴ አትናው ደግሞ 8 ተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በሴቶችበተካሄደው 44ኛው በለንደኑ የሴቶች የማራቶን ውድድር  ኬንያዊቷ ፔሬስ  ጄፕቺርቺር አንደኛበመሆን ስታሸንፍ  «በሴቶች ብቻየተሮጠ » አዲስ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችላለች። ጄፕቺርቺር ውድድሩን ለማጠናቀቅ ሁለት ሰዓት ከ 16 ደቂቃ ከ 16 ሰከንድ ወስዶባታል።  

አስቀድሞ የአሸናፊ ትሆናለች የሚል  ግምት የተሰጣት ትዕግስት አሰፋ ሁለተኛ በመሆን አጠናቀዋል። ትግስት ውድድሩን ለምጨረስ የፈጀባት ጊዜ 2 ሰዓት ከ 16 ደቂቃ ከ 23 ሰከንድ ነበር፤ ሌላዋ ኬንያዊት  ጆሲሊን ጄፕኮስጌበ አብድ ሰከንድ ተበልጣ ሦስተኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች። በ 44 ኛው የለንደን ማራቶን ዓለም መገርቱ  4ኛ በመሆን ውድድርዋን ስታጠናቅቅ ትግስት ከተማ እና ያለም ዘርፍ ያለው  ትግስት አብርሀ  7፣  8 እና 10 ኝ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።

ለንደን ማራቶን
ለንደን ማራቶን ምስል Alishia Abodunde/Getty Images

በሌላ የማራቶን ዜና በ41ኛው የቪየና ከተማ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ጫላ ረጋሳ አሽናፊ ሆንዋል ።  ኬንያውያን አትሊቶችአስከትሎ የገባው የ 26 ዓመቱ አትሌት   ጫላ ውድድሩን ለመጨረስ 2፡06፡35 ፈጅቶበታል። ሁለተኛ  እና ሦስተኛ በመሆን ኬንያውያኑ በርናርድ ሙአ እና አልበርት ካንጎጎ  ከኬንያ ሁለተኛ  እና ሦስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።

የምስራቅ አፍሪቃ አትሊቶች በበላይነት ባጠናቀቁት 41ኛው የቪይና ማራቶን ውድድር  በሴቶች ዘርፍ  ኤርትራዊቷ ናዝሬት ወልዱ አንደኛ ወጥታለች  ኬንያዊያን አትሊት  ፌዝ ቼብኮች እና ሬቤካ ታኑኢ 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል።

ባለፈውሳምት በቻይና የተካሄደውን የBኤጂንግ ማራቶን ውድድር አሽናፊ ውጤት አዘጋጁ መሰረዙን አስታውቆዋል ልዪ ኮሚቲው ባሳልፍው ውሳኔ ሶስት አትሊቶች ሆን ብለው ፍጥነታቸውን በመቀነስ ቻይናውዩ አትሊት ሂ ሽን እንዲያሽንፍ ማድረጋቸውን በምርመራ ካርጋገጠ ቡሀዋል ነው ። በውድድሩምአሽናፊ የሆነው ቻይናዊ  ሂ ዥ  ኬንያውያን እናኢትዮጵያዊ አትሊቶ ች ፍጥነታቸውን በመቀነስ ሆነ ብለው ፍጥነታቸውን በመቀነስ  እንዲያሽንፍ ያደረጉት  የ 25 አመቲሂ ዥ  የያለፈው ዓመት ኤዥያን ማራቶን ወርቅ አሽነፊ ከመሆኑም ባሻገር የ ቻይናን ብሄራዊ ክብር ረወሰን የያዘ አትሌት  ነው።

እግር ኳዋስ  

በ22ኛ ሣምንቱን በያዘው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጨዋታ በሳምንቱ መጨረሻ  የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አንድ ለአንድ በመለያየት ነጥብ ተጋርተው ውጥተዋል። የኢትዮጵያ ቡና አንድ ጎል  በጨዋታ የተመዘገበ ሲሆን  ጎልዋም በአማኑኤል አድማሱ የተገኛች ነች። የመቻልን ቡድን ጎል ምንይሉ ወንድሙ በፍጹም ቅጣት አስመጥግቦታል። በተመሳሳይ  22 ኛዉ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሽንፎዋል። 

የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ  

የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ በሳምንቱ መጨረሻ  ጨዋታዎች  ሊቨርፑል ኤቨርተን ክርስታል ፓላስ እናአስቶን ቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሽንፈዋል። ሊጠናቀቅ የተቃረበው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሁንም መሪውን መለየት አስቸጋሪ ሆንዋል። 

የአዉሮጳ ሊግ አትላንታ ከ ሊቨርፑል
የአዉሮጳ ሊግ አትላንታ ከ ሊቨርፑልምስል Jonathan Moscrop/CSM via ZUMA Press/picture alliance

በሳምንቱ መጨረሻ በተደረገው የ34ኛው ሳምንት ጨዋታ ሊቨርፑል ተጋጣሚውን ፉልሀምን 3ለ 1 አሸንፏል። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው አጋማሽአንድ ለአንድ በሆነ ውጤት አቻ ሆነው እረፍት የወጡ ቢሆንም ከዕረፍት መልስ ሊቨርፑል ባስቆጠራቸው 2 ጎሎች አሽናፊ ሆንዋል፡፡

የዮርገን ክሎፕ ቡድን ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎምበ74 ነጥብ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር  እኩል ነጥብ በመያዝ በጎል ክፍያ ተበልጦ  ሁለተኛ ደረጃ ላይተቀምጧል፡፡ የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ተመሳሳይ ጨዋታዎች  ኤቨርተን ነቲግሀም ፎረስትን 2 ለ 0 አስቶንቪላቦርንማውዝን 3ለ1 ክርስታፓላስ ዊስትሀምን 5ለ2 በመርታት ሶስት ነጥብ ይዘው ወጥተዋል። 

የ 34ኛውን ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግን  አርሰናል እና ሊቨርፑል በኩል 74 ነጥብ በጎል ክፍያተላያይተው 1ኛ ና 2 ኛ ሆነው ሲመሩት  ማንችስተርሲቲ በ73 ነጥብ  ሦስተኛ አስቶን ቪላ በ 66 አራተኛደረጃ ላይ ይገኛል። ሉተን በ 25 ነጥብ 18ኛ በርንል በ 23 ነጥብ 19 ሽፊልድዩናይትድ በ 16 ነጥብ 20 ኛ በመሆን  የወርጅቀጠናውን ይዘዋል።  

ማንችስተር ሲቲ ቡድን
ማንችስተር ሲቲ ቡድን ምስል Stu Forster/Getty Images

ኤፍ ካፕ ማንችስተር ዪናትድ እና ማንችስተር ሲቲ ለዋንጫ ይፋለምሉ

ትልንት ኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ በተደርገ ፍልሚያ ማንችስተር ዪናይትድ ከ ኮቭረንተሪ  ጨዋታ እና በተጨማሪ ሰአት  ሳይሽናነፉ  3ለ3 በሆነ ውጤትበመለያየታቸው  አሽናፊውን ለመለያት በተደረወየመለያ ምት  ማንችስተር ዪናይትድ 4 ለ 2 አሽንፎዋል። ምንም እንኳን በደከመ አጨዋወት በመለያ ምትአሽናፊ የሆነው ማችስተር ዪናትድ  በቅጣይ ከተቀናቃኙማንችስተር ሲቲ ይገጥማል።

የጀርመን ቡንደስ ሊጋ
የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ምስል Carmen Jaspersen/dpa/picture alliance

ቡንደስ ሊጋ

በ ጀርመን ቡንደስ ሊጋ  የሳምቱ መጨረሻ ጨዋታ የ  ባየር ሊቨርኩሰን የማታማታ ነጥብ ተጋርቶ መውጣት ቡድኑ ሳይሽነፍ  ከሜዳ የውጣበትን  ሪኮርድ ለማስጠበቅ አስችሎታል። የብንዱስሊጋው ዋንጫ አስቀድም ባለድሉ ቢታወቅም።  በ 30ኛው ጀርመን ቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ግጥሚያ መርሀግብር መሰረት  በሩሲያ ዶርቱመንድ ከ  የባዬርን ሌቨርኩሰን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተላያይተው ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል ።ጆሴፕ ስታንሲክ በጨዋታው ማብቂያ ላይ ያስቆጠራት ጎል ባየር ሊቨርኩሰኖች ነጥብ ተጋርተው እንዲወጡ ብቻ ሳይሆን  ያለ ሽንፍት የያዙትን ጉዞ ለማስቀጠል አስችሎዋቸዋል 45 ጭዋታ ያል ሽንፈት ተጉዘዋል ።

 

ሃና ደምሴ

አዜብ ታደሰ