1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሴቶች ከኔ ተማሩ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 18 2016

ሎቨነስ እንደ እሷ ያሉ በደንብ የተገነቡ አካሎች ያሏቸው ወይዛዝርት እንዳሉ ገልጻ ፣ ወደ መድረክ ወጥተው አቅማቸውን እንዲያሳዩ ትመክራለች።

https://p.dw.com/p/4ZX8p

ከታንዛኒያ ሎቨነስ ታሪሞ ተዋወቁ ። የ37 ዓመቷ እንስት የሰውነት ቅርጽ ስፖርተኛ ስትሆን በማሕበረሰቡ ያለውን የሴቶች ልክ ያልሆነ አመለካከትን በመጋፈጥ በአገሯና በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ካሉ ሴት አትሌቶች አንዷ ለመሆን እየጣረች ነው። እ.ኤ.አ. በ2019 አገሯን ወክላ በሰውነት እርጽ ስፖርት  አሸንፋለች ። እነዚህ ሁሉ ነገሮች ቢኖሩም ሰዎች በሰውነቷ መልክና ቁመናዋ ምክንያት ሴት መሆኗን ለመቀበል ሁሌም ይቸገራሉ።  ወደ ሰውነት ቅርጽ ስፖርት ለመግባት ምን አነሳሳት ?
ሎቨነስ ታሪሞ
"ከልጅነቴ ጀምሮ ስፖርት እወድ ነበር ። እግር ኳስ ከጀመርኩ በኋላ አሁን የሰውነት እርጽ ግንባታ ስፖርት  እየሰራሁበት ወዳለው ጂምናዚየም ተዛወርኩ "።
ሰዎች "ዱሜ ጂኬ" ብለው የሚጠሯት ሲሆን በስዋሂሊ የወንድ መልክ ላላት ሴት የሚጠሩበት ነው ። ሆኖም ከእሷ ጋር በመቆም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎቿን የሚደግፉ ቤተሰቦቿ እፎይታን አግኝቶላታል ።
ሎቨነስ ታሪሞ
" እንደዚህ መባል አልወድም ፤ ምክንያቱም ወንድ ለመሆን አልፈልግም ። ሴት ስለሆንኩ ደስተኛ ነኝ ፤ እግዚአብሔር ሴት አድርጎ ስለፈጠረኝ አመሰግነዋለሁ ፡ ፡ ሰዎች ሁልጊዜ ይጠቋቆሙብኛል ፤ ሰዎች እንዴት እንደሚያዩኝ ግራ ይገባኛል ። በጣም ስለሚያገሉኝ ይበልጥ ይጎዳኛል "
ቪክቶሪያ ታሪሞ
እህት

"አንዳንድ ጊዜ አንድ ነገር ገዝታ ከሱቅ ሄጄ እንዳመጣው ስትልከኝ  ባለሱቁ ይደውልና 'ባልሽ የምትመርጪውን አንዳንድ ዕቃዎች ጥሎልሻል" ይለኛል ። አብዛኛውን ጊዜ ባለቤቴ ሳትሆን እህቴ እንደሆነች እነግራቸዋለሁ ። በዚህ ጊዜ ግን መረዳት ይጀምራሉ "።
በሰውነቷ ቅርጽ ምክንያት በሚደርስባት ማሸማቀቅ ምክንያት ከሚገጥማት ፈታኝ ሁኔታ በተጨማሪ በአካል ብቃት እንቅስቃሴና ስፖርት ለመካፈል ፈለጓን የተከተሉ ሴቶች ይኖሩ ይሆን?
ሎቨነስ ታሪሞ

" በጣም ብዙ ናቸው ። እኔ የሰውነት ቅርጽ ስፖርተኛ ሆኜ ብቅ ካልኩ በኋላ ብዙዎች ፍላጎት አሳይተዋል ። ብዙዎች እንደ እኔ መሆን ይፈልጋሉ ፤ ሌሎች ደግሞ እንደኔ ያሉ አሉ ግን እራሳቸውን ከሕብረተሰቡ ደብቀው ነው ያሉት "

"እርስ በርሳችን እንግባባለን ፤ ምክንያቱም እሱ እኔን የወደደኝ በዚህ ሁኔታዮን ነው ፤ እኔም ከእሱ ጋር የምኖረው ለዚህ ነው ። ስለ ምንም ጉዳይ ግድ የለኝም ። እወደዋለሁ ፤ ደግሞም ይወደኛል ። ስለዚህ ሌሎች የሚሉትን አንሰማም ። እሱ የኔ ብቻ ነው ። "
ሎቨነስ እንደ እሷ ያሉ በደንብ የተገነቡ አካሎች ያሏቸው ወይዛዝርት እንዳሉ ገልጻ ፣ ወጥተው በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲታዩ ትመክራለች። በአካላዊ ቁመናቸው ምክንያት እንዳይሸሹና በስፖርትም ሆነ በሌሎች የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ እንዳይሳተፉ ትመክራለች።