ሞሮኮ ታሪክ ሰራ፤ ጀርመን ድል አልቀናዉም
ሐሙስ፣ ሐምሌ 27 2015ማስታወቂያ
ለመጀመርያ ጊዜ በሴቶች የዓለም እግርኳስ ዋንጫ ጨዋታ አዉስትራልያ ላይ እየተሳተፈች ያለችዉ ሰሜን አፍሪቃዊትዋ ሀገር ሞሮኮ፤ ጥሎ ማለፍ በመድረስ ታሪክ ሠራች። ብዙ ተጠብቆ የነበረዉ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን እንደመክፈቻዉ የጎል ዝናብ ማዝነብ አቅቶት ለግማሽ ፍፃሜ ሳይደርስ ቀርቷል። ወደ ሀገሩ ለመመለስም ሻንጣዉን እየሸከፈ ነዉ።
የጀርመን ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ዛሬ ባደረገዉ ግጥምያ የቡድኑ አጥቂ አሌክሳንድራ ፖፕ ያስቆጠረችዉ አንድ ግብ ቡድኑ ከደቡብ ኮርያ ጋር አቻ ለመዉጣት ቢያስችለዉም ፤ ለግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ግን ሳያስችለው ቀርቷል። በተመሳሳይ ምድብ 8 የተመደበችው ሞሮኮ ኮሎምቢያን 1-0 ካሸነፈች በኋላ ከኮሎምቢያ ጋር ተያይዘው ለጥሎ ማለፍ ለማለፍ በቅተዋል። ቀደም ሲል የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ ጋር ባካሄደዉ የመክፈቻ ግጥምያ 6 – 0 ማሸነፉ አይዘነጋም። የጀርመን የሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች - ልክ በኳታር ላይ በተካሄደዉ የጀርመን የወንዶች የዓለም እግርኳስ ዋንጫ ተሳታፊዎች ሁሉ ለግማሽ ፍጻሜ ሳይደርሱ መራራውን ጉዞ ወደ ሀገራቸው ለማድረግ ተገደዋል።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ