1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሞትና እገታ የተጋለጡት ከጎንደር ወደ መተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሾፌሮች

ረቡዕ፣ ሰኔ 19 2016

አንድ አሽከርካሪ “በየቦታው ሰው ማገት፣ ይህን ያክል ሚሊዮን ብር አምጡ፣ ለማን አቤት እንደመንል ተቸግረናል፣ አንድ ሳምንት ባልሞላ ውስጥ ከማክሰኝት ወጣ ብሎ ሁለት ሾፌሮች ተገድለዋል፣ ፈረንጅ ውሀ ከምትባል ቦታም አንድ ሾፌር በቅርቡ በጥይት ተተኩሶበት ሞቷል፣ መተማ መንገድም አንድ የሚኒ ባስ አሽከርካሪ ተገድሏል፣ ” ብሏል፡፡

https://p.dw.com/p/4hY0N
Äthiopien  West Gondar und Metema
ምስል DW/Alemenew Mekonnen

ለሞትና እገታ የተጋለጡት ከጎንደር ወደ መተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሾፌሮች

በአማራ ክልል በተለይም በጎንደር አንዳንድ ዞኖች የሚሰሩ አሽከርካሪዎች በእገታ፣ በድብደባ ሲከፋም ደግሞ ለግድያ መጋለጣቸውን ተናገሩ፣ መንግስት  በበኩሉ መንገዶችና አሽከርካሪዎች ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው ይላል፡፡በአማራ ክልል ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በሹፍርና ስራ ላይ የተሰማሩ ወገኖች በየመንገዱ እየታገቱ ከአቅማቸው በላይ ገንዘብ እንደሚጠየቁ፣ እንደሚደበደቡና እንደሚገደሉ ተናግረዋል፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ስራ እስከማቆም መድረሳቸውን ነው ለዶይቼ ቬሌ በስልክ የተናገሩት፡፡

አስተያየታቸውን ከሰጡን አሽከርካሪዎች መካከል አንዱ የደረሰበትን ችግር እንደሚከተለው አስረድቷል፡፡“... እኔ አሁን ስራ አቁሜያለሁ፣ "ምን አለ ልጆቻችንን ብናሳድግበት…?" የሾፌሮች ተማጽኖከምበላ ይቅርብኝ ብየ ከአገሬ ላይ ጫማ እየጠረግሁ ብኖር ይሻለኛል፣ ጋይንት ወጣ ካልክ ጀምሮ በየኪሎሜትሩ ወይ ትደበደባለህ፣ ወይ ትታገታለህ፣ ወይ ትገደላለህ፣ እኔ አሁን ተደብድቤ ነው የመጣሁት ጠርጥራ የምትባል ቦታ አለች ክምር ድንጋይ አካባቢ 2000 ብር አምጣ አሉኝ ሰጠኋቸው፣ ጀርበየን አንገቴን በሰደፍ ደበደቡኝ ሲበቃቸው ትተውኝ ሄዱ ብሩን ይዘው፣ ዓለም በር ከሚባል ቦታ ደግሞ አንድ ጓደኛችን የሚነዳውን መኪና ጎማ በጥይት አስተንፍሰው ልጁን ይዘውት ሄዱ፣ እሱን አልፈን መጥተን እንፍራንዝ ከሚባል ቦታ ቁልቋል በር ላይ አሁንም አንድ የጓደኛችን መኪና ጎማውን በጥይት አስተነፈሱት፣ በተነፈሰው ጎማ እነዳ መኪናው ሲቆም አሽከርካሪው በጫካ ውስጥ አልፎ ነብሱን አድኗል፡፡ ” ብሏል፡፡

ሌላ አሽከርካሪም እንደዚየአማራ ክልል ሾፌሮች ሮሮ ሁ ማገቱና መደብደቡ፣ መገደሉ ተበራክቷል ይላል፡፡“በየቦታው ሰው ማገት፣ ይህን ያክል ሚሊዮን ብር አምጡ፣ ለማን አቤት እንደመንል ተቸግረናል፣ አንድ ሳምንት ባልሞላ ውስጥ ከማክሰኝት ወጣ ብሎ ሁለት ሾፌሮች ተገድለዋል፣ ፈረንጅ ውሀ ከምትባል ቦታም እንዲሁ አንድ ሾፌር በቅርቡ በጥይት ተተኩሶበት ሞቷል፣ መተማ መንገድም አንድ የሚኒ ባስ አሽከርካሪ ተገድሏል፣ ሁመራ መስመር፣ ሙሴባምብና ሳንጃ መካከል፣ ከፈረስ መግሪያ እስከ ሙሴባምብ እገታ መደበኛ ስራ ሆኗል፡፡” ነው ያለው፡፡

አማራ ክልል መተማ
አማራ ክልል መተማ ምስል Alemnew Mekonnen

ከደቡብ ጎንደር ዞን አስተያየት የሰጠን አሽከከርካሪም ችግሩ እየሰፋ መምጣቱን ገልጧል፡፡ አክሎም፣ “ከፀዳ ጀምሮ እስከ ወረታ መገንጠያ፣ ከወረታ መገንጠያ እስከ ጋይንት ባለው መስመር መስራት አልተቻለም፣ ያለው ነገር ተስፋ ያስቆርጣል፣ ዓላማው ሊገባን አልቻለም፣ በአካባቢው እንቅስቃሴ እንዲቆም ይሁን ሾፌር ጠል ህብረተሰብ ተፈጥሮ ይሆን ዓላመው ሊገባን አልቻለም፡፡ በነዚህ   10  ቀናት ውስጥ ፈረንጅ ውሀ አካባቢ 3 ያክል አሽከርካሪዎች ተገድለዋል፡፡ ”ለእገታ የሚዳረጉት አገር አቋራጭ ሾፌሮች አቤቱታ

የደቡብ ጎንደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ ግን ችግሮች ይደርሳሉ ተብለው በተጠቀሱ የዓለም ብርና ጋሳ አካባቢዎች በቂ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ስለሚኖሩ ስሞታው ተጋኗል ብለዋል፣ አንዳንድ ሾፌሮች ከህገወጥ ሰዎች ጋር በመገናኘት የመኪናው አሰሪ መስሪያ ቤት ገንዘብ እንዲከፍል የማድረግ ስራ ይሰራሉ ሲሉም ተከላክለዋል፣ ሆኖም በቂና አስተማማኝ ጥበቃ መኖሩን ነው ያስረዱት፡፡በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ሞገስም ከገንዳ ውሀ እስከ ጎንደር ያለው አውራ ጎዳና ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት ነው ብለዋል፡፡

ሰኔ 9/2016 ዓ ም አንዲት የሱዳን ስደተኛን ጨምሮ 2 ኢትዮጵያዉያንን መንገድ ላይ ተሸከርካሪ አስቁመው ግድያ ከፈፀሙት ተጠርጣሪዎች መካከልም የተወሰኑት መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ