የቱርኩ ፕሬዚዳንት ጀርመንን ለመጎብኘት በርሊን ገቡ
ዓርብ፣ ኅዳር 7 2016ማስታወቂያ
የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬጄፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጀርመንን ለመጎብኘት መዲና በርሊን ገቡ። ከሦስት ዓመት ወዲህ ኤርዶጋን ወደ ጀርመን ሲመጡ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ። የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት በጦርነቱ ያላቸዉ አቋም ከቱርኩ ፕሬዚደንት የተለየ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ወደ በርሊን የመጡት ፕሬዚዳንቱ በተለያዩ ጉዳዮች ከመራሔ መንግሥቱ ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የቱርኩ ፕሬዚዳንት የበርሊን ጉብኝትን ተከትሎ በብዙ ፖሊሶች ጥበቃ ከተደረገላቸው በኋላ ከሦስት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓርብ ዕለት ጀርመንን ይጎበኛሉ። ከሌሎች የፌዴራል ግዛቶችና ከበርሊን የተሰባሰቡ ወደ 1500 የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጥበቃ ለማድረግ መሰማራታቸዉም ተገልጿል። እሁድ እለት የጀርመን እና የቱርክ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች ያደርጉታል የተባለዉ የወዳጅነት ጨዋታም ተሰርዟል። የቱርኩ ፕሬዚዳንት በሚገኙባቸዉ በመራሔ መንግሥቱ ቢሮ፤ እና በፕሬዚዳንቱ መቀመጫ በቤሌቩ ቤተ መንግሥት እንዲሁም በቱርክ ኤንባሲ አካባቢ ከፍተኛ የፀጥታ የደህንነት ጥበቃ እየተደረገ መሆኑም ተመልክቷል። የቱርክ ፕሬዚዳንት የጀርመን ጉብኝት አንድምታን በተመለከተ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለሚካኤልን አነጋግረናል።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ