ረቡዕ፣ ሰኔ 29 2014ዝነኛ የሙዚቃ አርቲስቶች፣ ሞቃታማ አየር እና ውኃማ ቦታ የሰመርጃም የሬጌ ድግስ መለያዎች ናቸው። በየዓመቱ በጎርጎሮሲያኑ የነሀሴ ወር የመጀመሪያው ሳምንት በሚውለው አርብ እስከ እሁድ የሚካሄደው ይኼው ድግስ ዘንድሮ 35ኛ ዓመቱን አክብሯል። በኮሎኝ ከተማ በሰው ሰራሹ ፍሩህሊንገር ሀይቅ ዙሪያ ሲካሄድ ደግሞ ሩብ ምዕተ ዓመት ሆነው። ይህ የዘንድሮውን ድግስ ለየት የሚያደርገው አንዱ ነገር ሲሆን ሌላው ደግሞ በኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ለሁለት ዓመት ያህል ከተቋረጠ በኋላ ዘንድሮ ሲካሄድ የመጀመሪያው መሆኑ ነው።