ፖለቲካ በፈረንሳይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን
ማክሰኞ፣ ሰኔ 11 2016ማስታወቂያ
በአውሮጳ የሰሞኑ የምክር ቤት ምርጫ ውጤት በፈረንሳይ ፖለቲከኞችን ብቻ አይደለም ያመሰው ። ጉዳዩ በፈረንሳይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ውስጥም ገብቷል ። በተለይ አፍሪቃዊ ዝርያ ያላቸው ታዋቂ ተጨዋቾች ቀኝ አክራሪ ዘረኞች ወደ ሥልጣኑ እንዳይመጡ ሲሉ ፖለቲካዊ ንግግር በማሰማት በፖለቲካ ውስጥ በቀጥታ መሳተፍ ጀምረዋል ።
የፈረንሣይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በአውሮጳ እግር ኳስ የምድብ ግጥሚያ ሰኞ፤ ሰኔ ቀን፣ 2016 ዓም ምሽት ከኦስትሪያ ጋ ተጋጥሞ እንደምንም 1 ለ0 አሸንፏል ። በእለቱ አምበሉ ኬሊያን እምባፔ አፍንጫው ላይ በደረሰበት ጉዳት ከሜዳ ለመውጣት ተገዷል ። እነ ኬሊያን እምባፔ እንዲሁም ማርኩስ ቱራምን ጨምሮ ጸረ ቀኝ አክራሪ ንግግር እያሰሙ ነው ። ለመሆኑ የፖለቲካ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት ወደ ፈረንሳይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ ሊገባ ቻለ? ከቃለ መጠይቁ ሙሉውን ይከታተሉ ።
ሐይማኖት ጥሩነህ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ