1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በበርሊን ተቃዉሞ ገጠማቸው

እሑድ፣ ኅዳር 9 2016

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በቡድን 20 “ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ” ጉባኤ ለመሳተፍ በርሊን ገብተዋል። ነገ ሰኞ በሚጀመረው ጉባኤ ለመሳተፍ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በርሊን ሲደርሱ ጀርመን በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዉያን ብርቱ ተቃዉሞ ገጥሟቸዋል።

https://p.dw.com/p/4Z9RI
Deutschland „Compact with Africa“-Gipfel in Berlin | Abiy Ahmed Ali und Olaf Scholz
ምስል Fabrizio Bensch/REUTERS

ጠቅላይ ሚንስትሩ በበርሊን ተቃውሞ ገጠማቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች የሚሳተፉበት የቡድን 20 “ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ” ጉባኤ ነገ ሰኞ በበርሊን ከተማ ይካሔዳል። በጀርመን አዘጋጅነት በሚካሔደው ጉባኤ ከአፍሪካውያን መሪዎች በተጨማሪ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሱላ ፎን ደርላየን፣ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩተ ይሳተፋሉ።

“ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ” በጎርጎሮሳዊው 2017 ጀርመን የቡድን 20 ፕሬዝደንት ሳለች የተጀመረ ነው። ጉባኤው ለውጥ ፈላጊ የአፍሪካ ሀገራትን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እና አጋሮችን በማሰባሰብ የልማት ጉዳዮችን የማስተባበር እና በኢንቨስትመንት ላይ ለመወያየት የተወጠነ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጉባኤው ለመሳተፍ በርሊን ሲደርሱ የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ተቀብለዋቸዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በርሊን ሲደርሱ ጀርመን በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዉያን ብርቱ ተቃዉሞ ገጥሟቸዋል።

ሙሉ ዘገባውን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ይልማ ሀይለሚካኤል 
ፀሀይ ጫኔ