1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥር 30 ቀን 2016 የዓለም ዜና

Eshete Bekeleሐሙስ፣ ጥር 30 2016

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመሥራት ላይ የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነሕ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ታዬ አጽቀሥላሴ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከአምስት ዓመታት ገደማ በፊት በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የተፈረመውን ሥምምነት አፍርሷል ሲል ከሰሰ። ከቱኒያዝ የባሕር ዳርቻ ጀልባ ሰጥማ ሕይወታቸውን ያጡ 13 ሱዳናውያን አስከሬን ተገኘ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ወደምትገኘው ራፋ ለመግባት እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ ሰጡ።

https://p.dw.com/p/4cC3z
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-News-DWcom

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።