የጠቅላይ ሚንስር ዐቢይ የካቢኔ ሹም ሽር
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 12 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የሚንስትሮች እና የሌሎች ኃላፊዎች ሹም ሽርና የሥልጣን ዝዉዉር አደረጉ።የጠቅላይ ሚንስትሩ ፅሕፈት ቤት ዛሬ እንዳስታወቀዉ በቅርቡ ከፓርቲ ስልጣናቸዉ በታገዱት በመከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ ምትክ አዲስ መከላከያ ሚንስትር ሾመዋል።የአዲስ አበባ አስተዳደርን በምክትል ከንቲባነት ማዕረግ ሲመሩ የነበሩትን ታከለ ኡማን፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትር አድርገዉ ሾመዋቸዋል።የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር የነበሩት ፕሮፌሰር ኂሩት ወልደማርያም የጠቅላይ ሚንስትሩ የማሕበራዊ ዘርፍ አማካሪ-ሚንስትር፣ የጠቅላይ ሚንስትሩ የፕረስ ጉዳይ ኃላፊ ንጉሱ ጥላሁን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚንሽነር ሆነዋል።ጠቅላይ አቃቢት ሕግ አዳነች አቤቤን በሌላ ሰዉ ሲተኩ፣ የአዲስ አበባን የምክትል ከንቲባነት ስልጣን ይዘዋል።የከተማይቱ ምክር ቤት ከሁለት ሰዓት በፊት ባደረገዉ አስቸኳይ ስብሰባ የአዲሲቱን ምክትል ከንቲባ ሹመት በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል።ከተሰበሰቡት 85 የምክር ቤት አባላት መካከል 77ቱ ሹመቱን ሲደግፉ፣ 6ቱ ተቃዉመዋል፣ ሌሎች ሁለት ደግሞ ድምፃቸዉን አቅበዋል።አዲሲቱ ምክትል ከንቲባ ቃለ መሐላ ፈፅመዉ፣ የከተማይቱን ቁልፍ ከቀድሞዉ ምክትል ከንቲባ ከታከለ ኡማ ተረክበዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ