1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የአንድነት ቀን

ማክሰኞ፣ መስከረም 24 2015

የሁለቱ ጀርመኖች መዋሃድ ጀርመን አሁን ለደረሰችበት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ እድገት ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ይነገራል። በመሆኑም ጀርመኖች ቀኑን በታላቅ ድምቀ በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 3 የሃገሪቱ ብሔራዊ በዓል ሆኖ በተለያዩ ዝግጅቶች ያከብሩታል።

https://p.dw.com/p/4Hitv
Mauergedenken Berlin
ምስል AP

የጀርመን የአንድነት ቀን

  ምስራቅና ምዕራብ ተብለው በሁለት ጎራ ተከፍለው የነበሩት ሁለቱ ጀርመኖች የበርሊኑ ግንብ ተንዶ አንድ የሆኑበትን የጀርመን የአንድነት ቀን በመላ ጀርመን ትላንት ተከብሯል። ይህን ቀን በተመለከተ የታሪክ ሙሁርና ተመራማሪ እንዲሁም የበርካታ ታሪካዊ መጻህፍት ደራሲ ዶክተር ልዑል አስፋወሰን አስራተን እንግዳችን ናቸው አብራችሁን ሁኑ መልካም ቆይታ።     
የታሪክ ሙሁርና ተመራማሪ ዶክተር ልዑል አስፋወሰን አስራተ ነበሩ ትላንት ስለተከበረው የጀርመን አንድነት ቀን  ለጀርመኖች ከፍተኛ ትርጉም እንዳለው አጫውተውናል። 
ሁለቱ ጀርመኖች በርእዮተዓለም በሚፎካከሩ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አሸናፊዎች ሥር መውደቃቸው ብቻም ሳይሆን እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር  በ1961 ዓ.ም ሁለቱንም የሚያለያይ የበርሊን የግንብ አጥር ጭምር በመስራት ነበር ላይገናኙ የታቀደው። ከ40 ዓመትት ቦኋላ በወቅቱ የነበሩት የያኔዋ የተባበሩት የሶቭየት ሕብረት ፕረዚደንት የተሃድሶ ለውጥ አውጀው ስለነበር ከምዕራቡ ዓለም ጋ የተለሳለሰ አቋም ያራምዱ ጀመር። ይህ በምዕራቡና ምስራቁ ዓለም የነበረው ርእዮተዓለምን መሰረት ያደረገ ልዩነት መቀዛቀዝ ለጀርመኖች ውህደት እንደመልካም አጋጣሚ እንደሆነላቸው የታሪክ ሙሁሩ ዶክተር ልዑል አስፋወሰን አስራተ ይገልጻሉ።የሁለቱ ጀርመኖች መዋሃድ ጀርመን አሁን ለደረሰችበት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ እድገት ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ይነገራል። በመሆኑም ጀርመኖች ቀኑን በታላቅ ድምቀ በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 3 የሃገሪቱ ብሔራዊ በዓል ሆኖ በተለያዩ ዝግጅቶች ያከብሩታል። 
የሁለቱን ጀርመኖች  መዋሃድ  ለጀርመንም ሆነ ለአውሮፓ መጠናከር በርካታ ጠቀሜታ እንዳለው በሰፊው ይነገራል። ሆኖም ግን ውህደቱ በተለይ በሶሻሊስት ርእዮት ሥር ለቆዩት ምስራቅ ጀርመናውያን ያመጣላቸው ብዙ በጎ ነገሮች ቢኖርም የሚቀሩ ነገሮች እንዳሉ ይወራል። የታሪክ ሙሁርና ተመራማሪው ዶክተር ልኡል አስፋወሰን አስራተ ግን ይህን አይቀበሉም።
ትላንት ስለተከበረው የጀርመኖች ውህደት አስመልክተን ከታሪክ ሙሁርና ተመራማሪ ዶክተር አስፋወሰን አስራተ ጋ የነበረን ቆይታ በዚሁ ፈጸምን። 

Deutschland Geschichte Berlin Mauer Mütter mit ihren Kindern
ምስል ullstein - Hilde

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር 

እሸቴ በቀለ