የጀርመን ርእሰ ብሔር ስለ ቻይና የእንቅስቃሴ ገደብ
ረቡዕ፣ ኅዳር 21 2015ማስታወቂያ
ዳግም የኮሮና ወረርሽኝ ሥጋት ተደቅኖብኛል ያለችው ቻይና ኮቪድን ለማጥፋት በሚል የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ በእጅጉ የሚገድብ ደንብ ተግባራዊ አድርጋለች። በቻይና ሰሜን ምዕራብ የዢንጂያን ግዛት ኡሩምቂ በተባለ ከተማ በሚገኝ የመኖሪያ ሕንጻ የተከሰተ የእሳት አደጋ ዐሥር ሰዎች ተቃጥለው መሞታቸው በመላ ቻይና የተለያዩ ከተሞች ቁጣን ቀስቅሶዋል። ነዋሪዎችም ለተቃውሞ አደባባይ እንዲወጡ አድርጓል። የተቃውሞ ሰልፈኞች ፖሊስ መረጃ ይዞ እንዳይከሳቸው በሚል ለተቃውሞ ወደ አደባባይ ይዘው የወጡት ሌጣ ነጭ ወረቀቶችን ነው።
ሽታይንማየር፤ «በቻይና ያለዉ ሁኔታ አሳስቦኛል»
የጀርመን ርእሰ-ብሔር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር «የቻይና ሁኔታ እጅግ አሳስቦኛል» ብለዋል። በቻይና የሕዝቡ ተቃውሞ የማድረግ ዴሞክራሲያዊ መብት እንዲከበርም ጠይቀዋል። ርእሰ ብሔሩ ይህን እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ከዶይቸ ቬለ (DW) ቴሌቪዥን ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ