1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእንስቶቹ የቁጠባ እና ብድር ማኅበር በኬንያ

ዓርብ፣ ጳጉሜን 2 2010

በኬንያ ከሞምባሳ አጠገብ ኪሊፊ በተባለች አካባቢ የሚኖሩ እንስቶች የጠረጴዛ ባንክ በተሰኘ አሰራር ገንዘብ ቆጥበው ለሚፈልጉ አባላት ያበድራሉ። አሰራሩ ከኢትዮጵያው የእቁብ አሰራር ጋር ይቀራረባል። #77 በመቶው በተሰኘው መሰናዶ የማኅበሩን እንቅስቃሴ ይቃኛል።

https://p.dw.com/p/34Vcc
Karte Kenia Mombasa Englisch

የእንስቶቹ የቁጠባ እና ብድር ማኅበር በኬንያ

ከኬንያዋ ሞምባሳ ከተማ አጠገብ ኪሊፊ መንደር የሚኖሩ እንስቶች በየሳምንቱ የአቅማቸውን ያክል ገንዘብ ያጠራቅማሉ። አጣዳፊ ችግር የገጠመው አባል አሊያም ገንዘብ የሚፈልግ አባል ብድር ይወስዳል። የሴቶቹ ቡድን ቱማይኒ ብድር እና ቁጠባ ማኅበር ይባላል። ቱማይኒ የሚለው ቃል በስዋሒሊ ቋንቋ ተስፋ የሚል ትርጓሜ አለው። ከስምንት ዓመታት በፊት አስር አባላት ብቻ ቢኖሩትም በሒደት ግን የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ባደረገው ድጋፍ ወደ ማኅበር አድጎ ስድሳ አባላት አሉት። አሰራሩ በኢትዮጵያ እንደሚታወቀው እቁብ ያለ ነው።

በኬንያ ቴብል ባንኪንግ ወይም የጠረጴዛ ባንክ በሚል ይታወቃል። አባላት በጋራ ገንዘብ ቆጥበው የሚበደሩበት የአሰራር ሥርዓት ነው። በየወሩ አባላቱ ተሰብስበው የቁጠባ ገንዘባቸውን ያጠራቅማሉ። ከተቆጠበው ገንዘብ ለአጭር ጊዜ ወይም የረዥም ጊዜ ብድር መውሰድ ይችላሉ። አንዲት አባል የምትበደረው የገንዘብ መጠን የሚወሰነው በቆጠበችው መጠን ነው። ማርጋሬት ንያሌ እንደ ማኅበሩ እናት ይቆጠራሉ። ማኅበሩን በመመሥረታቸው በርካታ እንስቶች አባል እንዲሆኑ በማሳመናቸው ማማ ኪሪባ የሚል መጠሪያ አትርፈዋል። 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

ዲያና ዋንዮኒ/እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ