1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በአሜሪካ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 27 2015

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋያና አቻዉ ጋር ያደረገዉን ግጥሚያ የተመለከቱ ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያንና የእግር ኳስ ባለሙያዎች እንዳሉት ቡድኑ ዩናትድ ስቴትስን በመጎብኝቱና በግጥሚያዉ ባሳየዉ ዉጤት ተደስተዋል

https://p.dw.com/p/4Uk0y
USA Äthiopien/Fußball-Nationalmanschaft zu Gast in Virginia
ምስል Abebe Feleke/DW

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጋያና ባላጋራዉን 2 ለ0 አሸነፈ

ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የተጓዘዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከጋያና አቻዉ ጋር ላዉደን-ቨርጂኒያ ግዛት ዉስጥ ከጋያና ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጋር ባደረገዉ የወዳጅነት ግጥሚያ ተጋጣሚዉን 2 ለ ዜሮ አሸንፏል።ቡድኑ ወደ አትላንታ-ጆርጂያ ግዛት ተጉዞ የፊታችን ቅዳሜ ከአትላንታ ሮበርስ ቡድን ጋር ሁለተኛዉን ግጥሚያ ያደርጋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋያና አቻዉ ጋር ያደረገዉን ግጥሚያ የተመለከቱ ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያንና የእግር ኳስ ባለሙያዎች እንዳሉት ቡድኑ ዩናትድ ስቴትስን በመጎብኝቱና በግጥሚያዉ ባሳየዉ ዉጤት ተደስተዋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዩናይትድ ስቴትስን ሲገበኝና እዚያ ሲጫወት ያሁኑ የመጀመሪያዉ ነዉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቨርጂኒያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቨርጂኒያ ምስል Abebe Feleke/DW

አበበ ፈለቀ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ