1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ መርማሪ ቡድን በጓንታናሞ የእስረኞችን አያያዝ ተቸ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 20 2015

በጓንታናሞ ቤይ የዩናይትድ ስቴትስ እስር ቤት ታስረው ከሚገኙ 30 ሰዎች መካከል 19ቱ እስረኞ ለ20 ዓመታት በእስር ላይ ቢገኙም በአንድም ወንጀል ተከሰዉ የማያውቁ መሆናቸው እጅግ እንዳሳሰበዉ አንድ የተባበሩት መንግሥታት መርማሪ ቡድን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/4T8Fi
USA Kriminalität l Behandlung von Guantánamo-Insassen l Camp 5 Außenansicht
ምስል Thomas Watkins/AFP

በጓንታናሞ ቤይ የዩናይትድ ስቴትስ እስር ቤት ታስረው ከሚገኙ 30 ሰዎች መካከል 19ቱ እስረኞ ለ20 ዓመታት በእስር ላይ ቢገኙም በአንድም ወንጀል ተከሰዉ የማያውቁ መሆናቸው  እጅግ  እንዳሳሰበዉ አንድ የተባበሩት መንግሥታት መርማሪ ቡድን አስታወቀ።
ገለልተኛ የሆነዉ ይህ የተባበሩት መንግሥታት መርማሪ ቡድን ትናንት ሰኞ እንደገለፀዉ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በጓንታናሞ የባሕር ወሽመጥ በሚገኙዉ እስር ቤቱ የያዛቸዉ እስረኞች ላይ የፈጸመው ድርጊት "ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢሰብዓዊነት የጎደለው እና አሳፋሪ ነው።"
የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ዘጋቢ ፊዮኑዋላ ኒ አኦላይን እንደገለፁት በዩናይትድ ስቴትስ ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት 30 እስረኞች ላይ የሚደርሰው ሥቃይ "ከባድ እና ቀጣይነት ያለው" ሲሉ አሳሳቢነቱን ተናግረዋል።
ዘጋቢዋ  ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤትን የጎበኙት የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር እስር ቤቱ ከተከፈተ ከጎርጎረሳዉያኑ 2002 ዓመት ወዲህ አንድ የተባበሩት መንግሥታት መርማሪን እንዲጎበኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈቀደ በኋላ ነው።
የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ በጎርጎረሳዉያኑ መስከረም 2001 በኒው ዮርክ ፣ በዋሽንግተን እና በፔንሲልቬንያ ወደ 3,000 የሚጠጉ ሰዎች በአሸባሪ ጥቃት ከተገደሉ ወዲህ ፤ ለጥቃቱ ምላሽ  ለመስጠት የጓንታናሞን እስር ቤት በጎርጎረሳዉያኑ 2002 ዓመት መክፈታቸዉ ይታወሳል። እስር ቤቱ የተከፈተው የእስልምና አሸባሪዎች ተብለው የጠሯቸዉን ለፍርድ ለማቅረብ ነበር።

USA Kriminalität l UN-Sonderberichterstatterin Fionnuala Ni Aolain, Behandlung von Guantánamo-Insassen
የተባበሩት መንግሥታት መርማሪ ቡድን ፊዮኑዋላ ኒ አኦላይንምስል Bianca Otero/Zuma Wire/dpa/picture alliance

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ