የብሪታኒያ ተገን ጠያቂዎችን ወደ ርዋንዳ ለማጓጓዝ የያዘችው ዕቅድ
ሐሙስ፣ ሰኔ 9 2014ብርታኒያ በህገወጥ መንገድ የገቡ የምትላቸውንና የስደተኝነት ጥያቄይቸው ተቀባይነት ያላገኙትን ስደተኖች ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የያችዘው እቅድ በአውሮፓ የሰባዊ መብት ፍርድ ቤት ትዛዝ ለግዜው ታግዷል። አዲስ በተቀየሰው የስደተኞች ፖሊስ መሰረት በመጅመሪያ በረራ ክ130 በላይ ስደተኖችን ወደ ሩዋንድ ላመላክ ዝግጅት የነበር ቢሆንም፤ በፍርድ ቤት ተእዛዝ ብዙዎቹ እንዲቆዩ ተደርጎ ሰባት ብቻ ነበሩ ባለፈው ማክሰኞች ምሽት በ300፣000 ፓውንድ ኮንትራት በቀረበው ቦይንግ 767 አውሮፕላን የተሳፈሩት። ሆኖም ግን በመጨርሽው ሰአት የአውሮፓ የሰባዊ መብት ፍርድ ቤት በይግባኝ በቀረበለት ያንዱ ኢራቃዊ ተጓዥ ስደተኛ መዝገብ ላይ ያሳለፈው የእግድ ውስኔ በመድረሱ የብርታኒያ መንግስት ጉዞውን እንዲሰርዝ ተገዷል። ውሳኔው በመጭው ሀምሌ ወር የብርታኒያ ፍርድ ቤት በአገሪቱ የስደተኖች ፖሊስ ህጋዊነት ላይ የሚያስተላልፈው ውሳኔ ከመታወቁ በፊት ይግባኝ ባዩን ስደተኛ ወድሌላ አገር መላክ አይቻልም የሚል ሲሆን ይኸው ውሳኔ በሌሎቹም ስድስት ስደተኖች ላይም ተግባራዊ ሁኗል።
ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን ባለፈው ሚያዚያ ወር ወደ ብርታኒያ በህገወጥ መንገድ የገቡ ስደተኖችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችል ስምምነት ከሩዋንዳ መንግስት ጋር የተፈራረሙ መሆኑን በመግለጽ፤ ካለፈው ጥር ወር ወዲህ ወደ ብርታኒያ በህገወጥ መነግድ የገቡና የሚገቡ ስደተኖች ከ6000 ኪሎሜትር በላይ ወደ ምትርቀው ሩዋንዳ እየተላኩ ጉዳያቸው እዚያው የሚታይ መሆኑን አስታውቀው ነበር
ስምምነቱ ብርታኒያ በያመቱ 138 ሚሊዮን ኢሮ ለአምስት አመታት ያህል እንድትለግስ የሚጠይቅና ክብርታኒይ የሚላኩ ስደተኖቾችም በሩዋንዳ የስደተኝነት ጥይቄ እንዲያቀርቡ የሚፈቅድ፤ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ካገኘም በዚያው የኑሮ ማቋቁሚያ ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን የሚገልጽ ነው። ይህን ስደተኖችን በሌላ ሶስተኝ አገር እንዲሰፍሩ የሚያስገድደውን ፕሮግራም ጠቅላይ ሚኒስተር ጆንሰንና መንግስታቸው አላማው ስደተኖች በህገወጥ መንገድ ወደ ብርታኒያ እንዳይገቡ ለመካላክል ብቻ ሳይሆን፤ ይልቁንም ሰዎች በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪ ደላሎች እንዳይበበዘበዙና ህይወታቸው ለአደጋ እንዳይጋለጥ ለማድረግ ነው በማለት ይከራከራሉ ። ሆኖም ግን የሰባዊ መብት፤ የስደተኖችና የመንግስታቱ ድርጅት ፕሮግራሙ፤ ብርታኒያ የፈርመቻቸውን አለማቀፍ የደተኖችና የሰባዊ መብት ድንጋጌዎችን የሚጥስ ነው በማለት አጥብቀው ተቃውመውታል። የብርታኒያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፕርቲዎች፣ የየይምኖት መሪዎችና የማህበረሰብ አንቂዎችም ይህን የሚስተር ጆንሰንን እቅድ ኢሞርራልዊ ህገወጥና አሳፋሪም ነው በማለት በአደባባይ ጭምር ሲቃወሙት ተሰምተዋል። ስደተኖች የሚላኩባት ሩዋንዳ እራሷ በሰባዊ መብት ጥሰት የምትወቀስና ለስደተኖች አመቺ ልትሆን የማትችል በመሆኗ ወደዚያ የሚላኩ ስደተኖች ለችግር መጋለጣቸው እንደማይቀርም እይተገለጸ ነው የአለማቀፉ የሰባዊ መብት ድርጅት ሁማን ራይትስ ዎች የመካከለኛው አፍርካ ዳይሬክተር ሚስተር ሌዊስ ሙድጌ ወደ ሩዋንድ የሚላኩ ስድተኖች ከሚያጋጣሟቸው ችግሮች ሁለቱን ይጠቅሳል። ድምጽ አንደኛው ስደተኖቹ የሚገቡበት የሩዋንዳ ስራት የስደተኖችን መብት የማያከብር ወይም ሊያከብር የማይችል ነው። ሁለተኛ ስደተኖቹ ባያያዛቸውና በሌሎች ጉዳዮች ቅሬታዎችን ለማቅረብ የሚችሉበት ድባብና ነጻነት የለም በማለት የዚያች አገር ሁኒታ ለስደተኖች የማያመች መሆኑን ግልጽ አድርጓል።
ይህ ተግባራዊነቱ ለግዜው የቆመው አከራክሪ የሚስተር ጆንሰን መንግስት ዕቅድ የሚቀጥል ወይም የሚቀለበስ ስለመሆኑ ገና አልታወቀም። በዕርግጥ ይህ አይነቱ ስደተኖችን ዳግም ወደሌላ አገር ማሰደድ በእስሬልና አውስትራሊያ ተሞክሮ ውጤት እንዳላስገኘ ነው የሚታወቀው። የብርታኒያ መነግስት ግን አሁን እቅዱ የታገደበትን ሁኒታ አስወግዶ ተግባራዊ እንደሚያደርገው ነው እየገለጸ ያለው። የህዝብ አስተያያት መመዘኛዎች 44 ከመቶው ብሪታናዊ ዕቅዱን እንደሚደግፍና 40 ከመቶው ብቻ እንደሚቃወም የሚጠቁሙ ሲሆን፤ ታዛቢዎች እንደሚሉት ይህ ሁኒታ ጠቅላይ ሚስተር ጆንሰንና መንግስታቸውን በዕቅዳቸው እንዲገፉ ሊያበረታታቸው ይችላል።
ገበያው ንጉሴ
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ