ትምህርት
ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች
ማስታወቂያ
«በቂ ዝግጅት አድርጌያለሁ» የምትለው ፌቨን ከዚህ ቀደም የተሰጡ ፈተናዎችን በመከለስ እየተዘጋጀች መሆኗን ትናገራለች። ንፁህ ደግሞ ወላጆች ልጆቻቸውን መደገፍ እና ለሴት ተማሪዎች እቤት ውስጥ ያለውን ጫና መቀነስ አለባቸው ትላለች። የድሬደዋ ቤተ መዛግብት እና መፃህፍት አስተባባሪ ኤርሚያስ ታደሰ ለዶይቸ ቬለ እንደገለፁት «በርካታ ሴት ተማሪዎች ከቤት የሚገጥማቸውን ጫና ተቋቁመው በመምጣት እያነበቡ ነው» ይላሉ። የድሬደዋ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊዲያ መለስ እራሷ ከተፈታኞቹ መካከል ናት። ባላት ክፍት ጊዜ የ12ኛ ክፍል ሴት ተፈታኞችን አነጋግራለች።
ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ