ተፈጥሮ እና አካባቢ አፍሪቃዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: "ተፈጥሮን እንንከባከብ በኢትዮጵያ"To view this video please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 videoተፈጥሮ እና አካባቢ አፍሪቃ7 ታኅሣሥ 2014ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 7 2014ልእልና ኃይሉ የ13 ዓመት ታዳጊ ናት።ታዳጊዋ ተፈጥሮን እንንከባከብ በኢትዮጵያ Nature Lovers of Ethiopia የተባለ የተፈጥሮ ተንከባካቢ ንቅናቄ መስራች እና መሪ ናት። መሰል ዝንባሌ ያላቸውን 10 ተማሪዎች ከጎኗ በማድረግ ንፁህ አካባቢን የመፍጠር እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች። #GOGREENTOBREATHCLEAN” በሚል መርህ ዓለምአቀፍ የአካባቢና አየር ብክለት ጉዳዮች ላይ እውቀት የማስጨበጥ ስራም ትሰራለች::https://p.dw.com/p/44NSLማስታወቂያልእልና ታዳጊ ተማሪ ጓደኞቿ ጋር የአትክልት ቦታ እንክብካቤን፣ ታዳሽ ቁሶችን የመፍጠር እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን ማፅዳትን የመሳሰሉ ተግባራትን ይሰራሉ። በዚህም እሷ የምትማርበትን ጨምሮ ሌሎች 9 ትምህርት ቤቶች ልእልናን እንቅስቃሴ አምነውበት ተቀላቅለዋታል። ዘገባ: ሱሙያ ሳሙኤል ቪዲዮ: ሰለሞን ሙጬ