የ«ስትሪንግ አርት»ተሰጥዎ ያላቸው ቤዛዊት እና ናርዶስ
ዓርብ፣ የካቲት 26 2013ማስታወቂያ
የ12 ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት ቤዛዊት እና ናርዶስ ይህን ጥበብ በመጠቀም በጠፍጣፋ ጣውላ ላይ ባለቀለማት ክሮችን በመጠቀም በተጥሮዋዊ፣ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስዕሎችን ያዘጋጃሉ። «መጀመሪያ ላይ ስለ ስትሪንግ አርት ኢንተርኔት ላይ ነው መረጃውን ያገኘነው። ስንጀምር ብዙ እንሰራለን ብለን አልነበረም። ለጓደኛችን ስጦታ ለመስጠት ብለን ነው የሞከርነው» ትላለች ናርዶስ። ቤዛዊት ቤተሰቦቻቸው እየደገፏቸው እንደሆነ ትናገራለች« ትዛዝ ካለን በዕረፍት ጊዜያችን እንሰራለን» ትላለች። ሰዎች ስራችንን ያደንቁልናል የሚሉት እነዚህ ወጣቶች ከሚገዛው ሰው ይልቅ ስራቸውን የሚያደንቅላቸው ሰው እንደሚበልጥ ይናገራሉ። አሁን አሁን በትዕዛዝ ይሰራሉ፣ ይሸጣሉ። ወደፊትም በዚህ ችሎታቸው ሊገፉበት ይፈልጋሉ።
ሊሻን ዳኜ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ/ልደት አበበ