1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከመቐለው ስልፍ ጋር በተገናኘ የታሰሩ የተቃዋሚፓርቲ አመራሮች ከእስር መለቀቃቸዉ

ሰኞ፣ ጳጉሜን 6 2015

ከመቐለው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው ፍርድቤት እንዲፈተቱ የወሰነባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፥ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሦስት ቀናት በኃላ ለቀናት ዛሬ ማምሻው ተለቀቁ። በሰልፉ እና ከሰልፉ በኃላ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈፀሙ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/4WCuo
ከመቐለው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው ፍርድቤት እንዲፈተቱ የወሰነባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፥ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሦስት ቀናት በኃላ ተለቀቁ
ከመቐለው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው ፍርድቤት እንዲፈተቱ የወሰነባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፥ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሦስት ቀናት በኃላ ተለቀቁ ምስል Million Hailesilassie/DW

በመቐለ ከተደረገው እና በፓሊስ በሐይል ከተበተነው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት፣ የማሕበረሰብ አንቂዎች፣ የሰልፊ ተሳታፊዎች ከቀናት እስር በኃላ በአብዛኛው ተፈትተዋል

ከመቐለው ስልፍ ጋር በተገናኘ የታሰሩ ሰዎች ከእስር መለቀቃቸዉ

ከመቐለው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው ፍርድቤት እንዲፈተቱ የወሰነባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፥ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሦስት ቀናት በኃላ ለቀናት ዛሬ ማምሻው ተለቀቁ። በሰልፉ እና ከሰልፉ በኃላ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈፀሙ ተገልጿል።

ባሳለፍነው ሐሙስ ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓመተምህረት በመቐለ ከተደረገው እና በፓሊስ በሐይል ከተበተነው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት፣ የማሕበረሰብ አንቂዎች፣ የሰልፊ ተሳታፊዎች ከቀናት እስር በኃላ በአብዛኛው ተፈትተዋል። ጳጉሜ 3 ቀን 2015 ዓመተምህረት ፍርድቤት ቀርበው 10 ሺህ ብር ዋስ በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ተፈርዶላቸው የነበሩ ስድስት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ለቀናት እስረኞቹ ፓሊስ ባለመልቀቁ በእስር የቆዩ ቢሆንም ዛሬ ድጋሜ ፍርድቤት በሰጠው ትእዛዝ ማምሻው በዋስ ተለቀዋል። 'ባዶ ስድስት' ከተባለው በመቐለ የሚገኝ እስርቤት ከተለቀቁ በኃላ አጭር ቃለምልልስ በስልክ የሰጡን የዓረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ፥ ፍርድቤት የዋስትና መብት ከሰጠን በኃላ ፓሊስ በማን አለብኝነት ለቀናት አስሮ አቆይቶናል ብለዋል።

ከመቐለው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው ፍርድቤት እንዲፈተቱ የወሰነባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፥ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሦስት ቀናት በኃላ ተለቀቁ
ከመቐለው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው ፍርድቤት እንዲፈተቱ የወሰነባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፥ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሦስት ቀናት በኃላ ተለቀቁ ምስል Million Hailesilassie/DW
ከመቐለው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው ፍርድቤት እንዲፈተቱ የወሰነባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፥ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሦስት ቀናት በኃላ ተለቀቁ።
ከመቐለው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው ፍርድቤት እንዲፈተቱ የወሰነባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፥ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሦስት ቀናት በኃላ ተለቀቁ።ምስል Million Hailesilassie/DW

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ሀያሉ ጎደፋይ፣ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አቶ ዓብለሎም ገብረሚካኤል፣ የባይቶና ከፍተኛ አመራሮች አቶ ክብሮም በርሃ እና ኪዳነ አመነ፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገቡ ዛሬ በዋስ ከተለቀቁ የተቃዋሚ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው። ሌላው ከሰልፉ ጋር በተያያዘ ለተከታታይ ቀናት እስር ላይ የቆየው እና ከፍተኛ ድብደባ የደረሰበት ጋዜጠኛ ተሻገር ፅጋብም ዛሬ ጠዋት በነፃ ተለቋል። ጋዜጠኛው ሰለቆይታው ይናገራል።

በቀጣይ በእርሱ እና ሌሎች ላይ ከፍተኛ የመብት ጥሰት የፈፀሙትን ለመክሰስ መዘጋጀቱ ጋዜጠኛ ተሻገር ፅጋብ ጨምሮ ገልፆልናል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ